ዘፍጥረት 40:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 የእንጀራ አበዛዎቹ አለቃም ሕልሙን በመልካም እንደ ተረጐመለት በአየ ጊዜ ዮሴፍን እንዲህ አለው፥ “እኔም ደግሞ ሕልም አይች ነበር፤ እነሆም፥ ሦስት መሶብ ነጭ እንጀራ በራሴ ላይ ነበረ፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 የእንጀራ ቤት አዛዡም፣ ለመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ሕልም፣ የተሰጠው ፍች ደስ የሚያሰኝ መሆኑን ሲሰማ፣ የራሱን ሕልም ለዮሴፍ እንዲህ ሲል ነገረው፤ “እኔም ደግሞ ሕልም አይቻለሁ፤ ሦስት መሶቦች በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 የእንጀራ ቤት አዛዡም፥ ለመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ሕልም፥ የተሰጠው ፍቺ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን ሲሰማ፥ የራሱን ሕልም ለዮሴፍ እንዲህ ሲል ነገረው፤ “እኔም ደግሞ ሕልም አይቻለሁ፤ ሦስት መሶቦች በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 የእንጀራ ቤት ኀላፊውም ዮሴፍ ለወይን ጠጅ አሳላፊው ሕልም የሰጠው ትርጒም መልካም መሆኑን ባየ ጊዜ፥ የእርሱንም ሕልም ለዮሴፍ እንዲህ ብሎ ነገረው፤ “እኔም በበኩሌ ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ ‘ሦስት መሶብ እንጀራ በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 የእንጀራ አበዛቹ አለቃም ሕልሙን በመልካም እንደ ተረጎመ ባየ ጊዜ ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ እኔም ደግሞ ሕልም አይቼ ነበር እነሆም ሦስት መሶብ ነጭ እንጀራ በራሴ ላይ ነበረ፤ 参见章节 |