Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እር​ስ​ዋም “ወንድ ልጅ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ኘሁ” አለች። ደግ​ሞም ወን​ድ​ሙን አቤ​ልን ወለ​ደ​ችው። አቤ​ልም በግ ጠባቂ ሆነ፤ ቃየ​ልም ምድ​ርን የሚ​ያ​ርስ ሆነ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች። አቤል የበግ እረኛ፣ ቃየንም ዐራሽ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ደግሞም፥ ወንድሙን አቤልን ወለደች። አቤልም በግ ጠባቂ ነበረ፥ ቃየንም መሬትን የሚያርስ ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ቀጥሎም የቃየልን ወንድም አቤልን ወለደች፤ አቤል የበጎች ጠባቂ ሆነ፤ ቃየል ግን ገበሬ ሆነ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች። አቤልም በግ ጠባቂ ነበረ፤ ቃየንም ምድርን የሚያርስ ነበረ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 4:2
19 交叉引用  

ስለ​ዚህ የተ​ገ​ኘ​ባ​ትን መሬት ያርስ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ደስታ ከሚ​ገ​ኝ​ባት ገነት አስ​ወ​ጣው።


እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “ወን​ድ​ሞ​ችህ በሴ​ኬም በጎ​ችን የሚ​ጠ​ብቁ አይ​ደ​ሉ​ምን? ወደ እነ​ርሱ እል​ክህ ዘንድ ና” አለው። እር​ሱም፥ “እሺ” አለው።


አዳ​ምም ሚስ​ቱን ሔዋ​ንን ዐወ​ቃት፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ ቃየ​ል​ንም ወለ​ደ​ችው።


ከብዙ ቀን በኋ​ላም እን​ዲህ ሆነ፤ ቃየል ከም​ድር ፍሬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረበ፤


ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ወን​ድ​ሞች፥ “ሥራ​ችሁ ምን​ድን ነው?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም ፈር​ዖ​ንን፥ “እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ፥ አባ​ታ​ች​ንም ከብት ጠባ​ቂ​ዎች ነን” አሉት።


ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፤ ወይ​ንም ተከለ።


ሚስ​ትህ በቤ​ትህ እል​ፍኝ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ያ​ፈራ ወይን ትሆ​ና​ለች፤ ልጆ​ች​ህም በማ​ዕ​ድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወ​ይራ ተክል ይሆ​ናሉ።


ሙሴም የአ​ማ​ቱን የም​ድ​ያ​ምን ካህን የዮ​ቶ​ርን በጎች ይጠ​ብቅ ነበር፤ በጎ​ቹ​ንም ወደ ምድረ በዳ ዳርቻ ነዳ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ​ቹን ከመ​ከ​ተል ወሰ​ደኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ሂድ፥ ለሕ​ዝቤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ትን​ቢት ተና​ገር አለኝ።


ዓለም ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ እስ​ከ​ዚ​ህች ትው​ልድ ድረስ ስለ ፈሰ​ሰው ስለ ነቢ​ያት ሁሉ ደም ይበ​ቀ​ላ​ቸው ዘንድ፥


ከአ​ቤል ደም ጀምሮ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና በቤተ መቅ​ደሱ መካ​ከል እስከ ገደ​ሉት እስከ ዘካ​ር​ያስ ደም ድረስ እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ ከዚች ትው​ልድ ይፈ​ለ​ጋል።


እና​ን​ተስ ከአ​ባ​ታ​ችሁ ከሰ​ይ​ጣን ናችሁ፤ የአ​ባ​ታ​ች​ሁ​ንም ፈቃድ ልታ​ደ​ርጉ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እርሱ ከጥ​ንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእ​ው​ነ​ትም አይ​ቆ​ምም፤ በእ​ርሱ ዘንድ እው​ነት የለ​ምና፤ ሐሰ​ት​ንም በሚ​ና​ገ​ር​በት ጊዜ ከራሱ አን​ቅቶ ይና​ገ​ራል፤ ሐሰ​ተኛ ነውና፤ የሐ​ሰ​ትም አባት ነውና።


የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፤ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።


ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለ ምንስ ገደለው? የገዛ ሥራው ክፉ፥ የወንድሙም ሥራ ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።


ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ።


跟着我们:

广告


广告