Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 39:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ያለ​ው​ንም ሁሉ ለዮ​ሴፍ በእጁ አስ​ረ​ከ​በው፤ ከሚ​በ​ላ​ውም እን​ጀራ በቀር ምንም የሚ​ያ​ው​ቀው አል​ነ​በ​ረም። ዮሴ​ፍም መልኩ ያማረ፥ ፊቱም እጅግ የተ​ዋበ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህ ጲጥፋራ ባለው ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጠው፤ የቀረበለትንም ከመመገብ በቀር፣ ማንኛውንም ጕዳይ በዮሴፍ ላይ ጥሎ ነበር። ዮሴፍ ጥሩ ቁመና ያለውና መልከ መልካም ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ስለዚህ ጲጥፋራ ባለው ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጠው፤ የቀረበለትንም ከመመገብ በስተቀር፥ ማናቸውንም ጉዳይ በዮሴፍ ላይ ጥሎ ነበር። ዮሴፍ ጥሩ ቁመና ያለውና መልከ መልካም ነበር፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ስለዚህ ጶጢፋር ያለውን ንብረት ሁሉ በዮሴፍ ቊጥጥር ሥር አደረገ፤ ጶጢፋር ከሚመገበው ምግብ በስተቀር የሚያውቀው ምንም ነገር አልነበረም። ዮሴፍ ቁመናው የተስተካከለ መልከ መልካም ሰው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ያለውንም ሁሉ ለዮሴፍ አስረከበ ከሚበላውም እንጀራ በቀር ምንም የሚያውቀው አልነበረም። የዮሴርም ፊቱ መልከ መልካምን ውብ ነበረ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 39:6
12 交叉引用  

ልያም ዓይነ ልም ነበ​ረች፤ ራሔል ግን መልከ መል​ካም ነበ​ረች፥ ፊቷም ውብ ነበረ።


የግ​ዞት ቤቱ ጠባ​ቂ​ዎች አለ​ቃም በግ​ዞት ቤት የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ምንም አያ​ው​ቅም ነበር፤ ሁሉን ለዮ​ሴፍ ትቶ​ለት ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ረና፤ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ ያቀ​ና​ለት ነበር።


ዮሴ​ፍም በጌ​ታው ፊት ሞገ​ስን አገኘ፤ እር​ሱ​ንም ደስ ያሰ​ኘው ነበር፤ በቤ​ቱም ላይ ሾመው፤ ያለ​ው​ንም ሁሉ በእጁ ሰጠው።


እር​ሱም እንቢ አለ፤ ለጌ​ታ​ውም ሚስት እን​ዲህ አላት፥ “እነሆ፥ ጌታዬ በቤቱ ያለ​ውን ሁሉ ለእኔ በእጄ አስ​ረ​ክ​ቦ​ኛል፤ በቤቱ ያለ​ው​ንም ምንም የሚ​ያ​ው​ቀው የለም፤


ለእ​ር​ሱም ለብ​ቻው አቀ​ረቡ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ለብ​ቻ​ቸው፤ ከእ​ርሱ ጋር ለሚ​በ​ሉት ለግ​ብፅ ሰዎ​ችም ለብ​ቻ​ቸው፤ የግ​ብፅ ሰዎች ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ጋር መብ​ላት አይ​ች​ሉ​ምና፥ ይህ ለግ​ብፅ ሰዎች እንደ መር​ከስ ነውና።


“በጥ​ቂት የሚ​ታ​መን በብዙ ይታ​መ​ናል፤ በጥ​ቂት የሚ​ያ​ም​ፅም በብ​ዙም ቢሆን ያም​ፃል።


ጌታ​ውም፦ መል​ካም፥ አንተ በጎ አገ​ል​ጋይ በጥ​ቂት የታ​መ​ንህ ስለ​ሆ​ንህ በብዙ ላይ እሾ​ም​ሃ​ለሁ፤ በዐ​ሥሩ ከተ​ሞች ላይ ተሾም አለው።


“ያን​ጊ​ዜም ሙሴ ተወ​ለደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊትም የተ​ወ​ደደ ሆነ፤ ለሦ​ስት ወርም በአ​ባቱ ቤት አሳ​ደ​ጉት።


ልኮም አስ​መ​ጣው፤ እር​ሱም ቀይ፥ ዐይ​ኑም የተ​ዋበ፥ መል​ኩም ያማረ ነበረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ይህ መል​ካም ነውና ተነ​ሥ​ተህ ዳዊ​ትን ቅባው” አለው።


ጎል​ያ​ድም ዳዊ​ትን ትኩር ብሎ አየው፤ ቀይ ብላ​ቴና፥ መል​ኩም ያማረ ነበ​ረና ናቀው።


跟着我们:

广告


广告