Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 38:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እር​ሱም፥ “ምን መያዣ ልስ​ጥሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “ቀለ​በ​ት​ህን፥ ኩፌ​ት​ህን፥ በእ​ጅህ ያለ​ውን በትር” አለች። እር​ሱም ሰጣ​ትና ከእ​ር​ስዋ ደረሰ፤ እር​ስ​ዋም ፀነ​ሰ​ች​ለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “ታዲያ ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እርሷም፣ “የማኅተም ቀለበትህን ከነማሰሪያው፣ እንደዚሁም ይህን በትርህን ስጠኝ” አለችው። የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣትና ዐብሯት ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 “ታዲያ ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እርሷም፥ “የማኅተም ቀለበትህን ከነማሰሪያው፥ እንደዚሁም ይህን በትርህን ስጠኝ” አለችው። የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣትና አብሯት ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እርሱም “ታዲያ፥ መያዣ የሚሆን ነገር ምን ልስጥሽ?” አላት። እርስዋም “የማኅተም ቀለበትህን ከነማሰሪያውና ይህን የያዝከውን በትር ስጠኝ” አለችው። ስለዚህ የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣትና ወደ እርስዋ ገባ፤ እርስዋም ፀነሰችለት

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እርሱም፦ ምን መያዣ ልስጥሽ? አላት። እርስዋም፦ ቀለበትህን አምባርህን በእጅህ ያለውን በትር አለች እርሱም ሰጣትና ከእርስዋ ደረሰ እርስዋም ፀነሰችለት።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 38:18
8 交叉引用  

“የፍ​የል ጠቦት ከመ​ን​ጋዬ እል​ክ​ል​ሻ​ለሁ” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “እስ​ክ​ት​ል​ክ​ልኝ ድረስ መያዣ ስጠኝ” አለ​ችው።


እር​ስ​ዋም ተነ​ሥታ ሄደች፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዋ​ንም አው​ልቃ የመ​በ​ለ​ት​ነ​ቷን ልብስ ለበ​ሰች።


ፈር​ዖን ቀለ​በ​ቱን ከእጁ አወ​ለቀ፤ በዮ​ሴ​ፍም እጅ አደ​ረ​ገው፤ የነጭ ሐር ልብ​ስ​ንም አለ​በ​ሰው፤ በአ​ን​ገ​ቱም የወ​ርቅ ዝር​ግ​ፍን አደ​ረ​ገ​ለት፤


“እኔ ሕያው ነኝ የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ቄም ልጅ ኢኮ​ን​ያን ሆይ፥ አን​ተን በሰ​ወ​ር​ሁ​በት ቀኝ እጄ እን​ዳለ ማሕ​ተም ነበ​ርህ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ግን እን​ደ​ማ​ት​ኖር እኔ ሕያው ነኝ፤” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤


የሕ​ዝቤ ልቡ​ና​ቸው ዝሙ​ትን፥ መጠ​ጥ​ንና ስካ​ርን ወደደ።


የም​ራ​ት​ህን ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የል​ጅህ ሚስት ናት፤ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን አት​ግ​ለጥ።


አባ​ቱም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን እን​ዲህ አላ​ቸው፦ ‘ያማሩ ልብ​ሶ​ችን ቶሎ አም​ጡና አል​ብ​ሱት፤ ለጣ​ቱም ቀለ​በት፥ ለእ​ግ​ሩም ጫማ አድ​ር​ጉ​ለት፤’


跟着我们:

广告


广告