Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 37:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ኑ፥ ለእ​ነ​ዚህ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን እን​ሽ​ጠው፤ እጃ​ች​ንን ግን በእ​ርሱ ላይ አን​ጣል፤ ወን​ድ​ማ​ችን ሥጋ​ችን ነውና።” ወን​ድ​ሞ​ቹም የነ​ገ​ራ​ቸ​ውን ሰሙት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ከዚህ ይልቅ ለእስማኤላውያን ነጋዴዎች እንሽጠው፤ እጃችንን ግን በርሱ ላይ አናንሣ። ምንም ቢሆንኮ ወንድማችን፣ ሥጋችን ነው” ወንድሞቹም በሐሳቡ ተስማሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ኑ፥ ለእስማኤላውያን እንሽጠው፥ እጃችንን ግን በእርሱ ላይ አንጣል፥ ወንድማችን ሥጋችንም ነውና።” ወንድሞቹም የእርሱን ነገር ሰሙት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እርሱ የሥጋ ወንድማችን ስለ ሆነ” በእርሱ ላይ ጒዳት ከምናደርስበት ይልቅ ለእነዚህ እስማኤላውያን ነጋዴዎች ብንሸጠው ይሻላል፤ ወንድሞቹም በዚህ ሐሳብ ተስማሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ኑ ለእስማኤላውያን እንሽጠው እጃችንን ግን በእርሱ ላይ አንጣል፥ ወንድማችን ሥጋችንም ነውና

参见章节 复制




ዘፍጥረት 37:27
15 交叉引用  

ላባም ያዕ​ቆ​ብን፥ “በእ​ው​ነት አንተ አጥ​ንቴ ሥጋ​ዬም ነህ፤ ከእኔ ጋር ተቀ​መጥ” አለው። አንድ ወር የሚ​ያ​ህ​ልም ከእ​ርሱ ጋር ተቀ​መጠ።


ሮቤ​ልም፥ “ደም አታ​ፍ​ስሱ፤ በዚች ምድረ በዳ ባለ​ችው ጕድ​ጓድ ጣሉት፤ ነገር ግን እጃ​ች​ሁን አት​ጣ​ሉ​በት” አላ​ቸው። ሮቤ​ልም እን​ዲህ ማለቱ ከእ​ጃ​ቸው ሊያ​ድ​ነ​ውና ወደ አባቱ ሊመ​ል​ሰው ነው።


እነ​ር​ሱም እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ ተባ​ባሉ፥ “በእ​ው​ነት ወን​ድ​ማ​ች​ንን በድ​ለ​ናል፤ እኛን በመ​ማ​ጠን ነፍሱ ስት​ጨ​ነቅ አይ​ተን አል​ሰ​ማ​ነ​ው​ምና፤ ስለ​ዚህ ይህ መከራ መጣ​ብን።”


እና​ንተ በእኔ ላይ ክፉ መከ​ራ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እን​ዲ​መ​ገብ ለማ​ድ​ረግ ለእኔ መል​ካም መከረ።


አሁ​ንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ነገር ለምን አቃ​ለ​ልህ? ኬጤ​ያ​ዊ​ውን ኦር​ዮን በሰ​ይፍ መት​ተ​ሃል፤ ሚስ​ቱ​ንም ለአ​ንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስ​ደ​ሃል፤ እር​ሱ​ንም በአ​ሞን ልጆች ሰይፍ ገድ​ለ​ሃል።


አሁ​ንም ሥጋ​ችን እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሥጋ፥ ልጆ​ቻ​ች​ንም እንደ ልጆ​ቻ​ቸው ናቸው፤ እነ​ሆም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችን ባሪ​ያ​ዎች ይሆኑ ዘንድ ሰጥ​ተ​ናል፤ ከሴ​ቶ​ችም ልጆ​ቻ​ችን ባሪ​ያ​ዎች ሆነው የሚ​ኖሩ አሉ፤ ታላ​ላ​ቆ​ችም እር​ሻ​ች​ን​ንና ወይ​ና​ች​ንን ይዘ​ዋ​ልና ልና​ድ​ና​ቸው አን​ች​ልም” የሚሉ ነበሩ።


እኔም፥ “ለአ​ሕ​ዛብ የተ​ሸ​ጡ​ትን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንን አይ​ሁ​ድን በፈ​ቃ​ዳ​ችን ተቤ​ዠን፤ እና​ን​ተስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ትሸ​ጣ​ላ​ች​ሁን? እነ​ር​ሱስ ለእኛ የተ​ሸጡ ይሆ​ና​ሉን?” አል​ኋ​ቸው። እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ መል​ስም አላ​ገ​ኙም።


“አባ​ቱን ወይም እና​ቱን የሚ​ሰ​ድብ በሞት ይቀጣ።


የተ​መ​ታው ግን አንድ ወይም ሁለት ቀን ቢቈይ ገን​ዘቡ ነውና አይ​ቀጣ።


ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?


“ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ?” እነርሱም ሠላሳ ብር መዘኑለት።


ቀረፋም፥ ቅመምም፥ የሚቃጠልም ሽቱ፥ ቅባትም፥ ዕጣንም፥ የወይን ጠጅም፥ ዘይትም፥ የተሰለቀ ዱቄትም፥ ስንዴም፥ ከብትም፥ በግም፥ ፈረስም፥ ሰረገላም፥ ባሪያዎችም፥ የሰዎችም ነፍሳት ነው።


ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ታላ​ቂቱ ልጄ ሜሮብ እነ​ኋት፤ እር​ስ​ዋን እድ​ር​ል​ሃ​ለሁ፤ ብቻ ጀግና ልጅ ሁን​ልኝ፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጦር​ነት ተጋ​ደል” አለው። ሳኦ​ልም፥ “የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ በእ​ርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእ​ርሱ ላይ አት​ሁን” ይል ነበር።


跟着我们:

广告


广告