Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 33:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ዔሳ​ውም፥ “ከእኔ ጋር ካሉ ሰዎች ከፍዬ ልተ​ው​ል​ህን?” አለ። እር​ሱም፥ “ይህ ለም​ን​ድን ነው? በጌ​ታዬ ዘንድ ሞገ​ስን ማግ​ኘቴ ይበ​ቃ​ኛል” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ዔሳው፣ “እንግዲያስ ከሰዎቼ ጥቂቶቹን ልተውልህ” አለው። ያዕቆብ ግን፣ “ለምን ብለህ ጌታዬ? በአንተ ዘንድ ሞገስ ማግኘቴ ብቻ ይበቃኛል” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ዔሳውም፥ “ከእኔ ጋር ካሉት ሰዎች ከፍዬ ልተውልህን” አለ። እርሱ ግን፥ “ይህ ለምንድን ነው? በጌታዬ ዘንድ ሞገስን ማግኘት ይበቃኛል” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ዔሳውም “እንግዲያውስ ከእኔ ሰዎች ጥቂቶቹን ከአንተ ጋር ላስቀርልህ” አለው። ያዕቆብ ግን “በጌታዬ ፊት ሞገስ ካገኘሁ ሌላ ምንም ነገር አያስፈልገኝም” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ዔሳውም፦ ከእኔ ጋር ካሉት ሰዎች ከፍዬ ልተውልህን? አለ። እርሱም፦ ይህ ለምንድር ነው? በጌታዬ ዘንድ ሞገስን ማግኘት ይበቃኛል አለ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 33:15
8 交叉引用  

የላ​ካ​ቸው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ ያዕ​ቆብ ተመ​ል​ሰው እን​ዲህ አሉት፥ “ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እር​ሱም ደግሞ ሊቀ​በ​ልህ ይመ​ጣል፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ።”


ዔሳ​ውም በዚያ ቀን ወደ ሴይር ተመ​ለሰ።


ሴኬ​ምም አባ​ቷ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ዋን እን​ዲህ አለ፥ “በፊ​ታ​ችሁ ሞገ​ስን በአ​ገኝ የም​ት​ሉ​ትን ሁሉ እሰ​ጣ​ለሁ።


እነ​ር​ሱም፥ “አንተ አዳ​ን​ኸን፤ በጌ​ታ​ች​ንም ፊት ሞገ​ስን አገ​ኘን፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ሆ​ና​ለን” አሉት።


ንጉ​ሡም ሲባን፥ “እነሆ፥ ለሜ​ም​ፌ​ቡ​ስቴ የነ​በ​ረው ሁሉ ለአ​ንተ ይሁን” አለው። ሲባም ሰግዶ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በፊ​ትህ ሞገ​ስን ላግኝ” አለ።


እርስዋም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ከባሪያዎችህ እንደ አንዲቱ ሳልሆን አጽናንተኽኛልና፥ የባሪያህንም ልብ ደስ አሰኝተሃልና በዓይንህ ሞገስ ላግኝ አለችው።


እር​ስ​ዋም፥ “ባር​ያህ በፊ​ትህ ሞገ​ስን አገ​ኘች” አለ​ችው። ሴቲ​ቱም መን​ገ​ድ​ዋን ሄደች፤ ወደ ቤት​ዋም ገባች፤ ከባ​ሏም ጋር በላች፤ ጠጣ​ችም ፤ ፊቷም ከዚያ በኋላ አዘ​ን​ተኛ መስሎ አል​ታ​የም።


ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህን ጠይ​ቃ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ይነ​ግ​ሩ​ሃል፤ አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ በመ​ል​ካም ቀን መጥ​ተ​ና​ልና ብላ​ቴ​ኖች በፊ​ትህ ሞገስ ያግኙ፤ በእ​ጅ​ህም ከተ​ገ​ኘው ለል​ጅህ ለዳ​ዊት እባ​ክህ፥ ላክ።”


跟着我们:

广告


广告