Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 32:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አን​ተም፦ ‘በር​ግጥ መል​ካም አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ፥ ዘር​ህ​ንም ከብ​ዛቱ የተ​ነሣ እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደ​ር​ጋ​ለሁ ብለህ ነበር።’ ”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ነገር ግን፣ አንተ ራስህ፣ ‘አበለጽግሃለሁ፤ ዘርህንም ሊቈጠር እንደማይቻል እንደ ባሕር አሸዋ አበዛዋለሁ’ ብለኸኛል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አንተም፦ ‘በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተነሣ እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ’ ብለህ ነበር።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ‘መልካም ነገር አደርጋለሁ፤ ዘርህንም ሊቈጠር እንደማይቻል እንደ ባሕር ዳር አሸዋ አበዛልሃለሁ’ ያልከውን አስታውስ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አንተም፦ በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተንሣ እንድማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ ብለህ ነበር።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 32:12
14 交叉引用  

ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብ​ትና በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዘር​ህም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይወ​ር​ሳሉ፤


የላ​ካ​ቸው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ ያዕ​ቆብ ተመ​ል​ሰው እን​ዲህ አሉት፥ “ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እር​ሱም ደግሞ ሊቀ​በ​ልህ ይመ​ጣል፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ።”


ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤ​ልም እንደ ባሕር አሸዋ ብዛት ብዙ ነበሩ፤ ይበ​ሉና ይጠ​ጡም፥ ደስም ይላ​ቸው ነበር።


ዘራ​ች​ሁን እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛ​ለሁ፤ ይህ​ች​ንም የተ​ና​ገ​ር​ኋ​ትን ምድር ሁሉ ለዘ​ራ​ችሁ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ይወ​ር​ሱ​አ​ታል ብለህ በራ​ስህ የማ​ል​ህ​ላ​ቸው ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህን አብ​ር​ሃ​ም​ንና ይስ​ሐ​ቅን ያዕ​ቆ​ብ​ንም ዐስብ።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ቍጥር እን​ደ​ማ​ይ​ሰ​ፈ​ርና እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠር እንደ ባሕር አሸዋ ይሆ​ናል፤ እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ “እና​ንተ ሕዝቤ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም” ተብሎ በተ​ነ​ገ​ረ​በት በዚያ ስፍራ የሕ​ያው አም​ላክ ልጆች ይባ​ላሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰው የሚ​ታ​ለል አይ​ደ​ለም። እንደ ሰው ልጅም የሚ​ዛ​ት​በት አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ያለ​ውን አያ​ደ​ር​ገ​ው​ምን? አይ​ና​ገ​ረ​ው​ምን? አይ​ፈ​ጽ​መ​ው​ምን?


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


ባናምነው፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።”


ስለ​ዚ​ህም ደግሞ በብ​ዛ​ታ​ቸው እንደ ሰማይ ኮከብ፥ እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠ​ርም በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ የነ​በ​ሩት የሞ​ተን ሰው እንኳ ከመ​ሰ​ለው ከአ​ንዱ ተወ​ለዱ።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተስ​ፋ​ውን ለሚ​ወ​ርሱ ሰዎች ምክ​ሩን እን​ደ​ማ​ይ​ለ​ውጥ ሊገ​ልጥ ወደደ፤ እን​ደ​ማ​ይ​ለ​ው​ጥም በመ​ሓላ አጸ​ናው።


እስ​ራ​ኤል ለሁ​ለት ይከ​ፈ​ላል፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም አይ​ሰ​በ​ሰ​ብም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ሰው የሚ​ጸ​ጸት አይ​ደ​ለ​ምና አይ​ጸ​ጸ​ትም” አለው።


跟着我们:

广告


广告