Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 31:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 ለአ​ንተ ቤት የተ​ገ​ዛ​ሁ​ልህ ዛሬ ሃያ አንድ ዓመት ነው፤ ዐሥራ አራት ዓመት ስለ ሁለቱ ሴቶች ልጆ​ችህ፥ ሰባት ዓመት ስለ በጎ​ችህ ተገ​ዛ​ሁ​ልህ፤ ደመ​ወ​ዜ​ንም ዐሥር ጊዜ ለዋ​ወ​ጥ​ኸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ሃያ ዓመት በቤትህ የኖርሁት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ዐሥራ አራት ዓመት ለሁለቱ ልጆችህ ብዬ አገለገልሁ፤ ስድስት ዓመት ስለ መንጋዎችህ ስል አገለገልሁ፤ ይህም ሆኖ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ ለዋውጠህብኛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 እነዚህን ሃያ ዓመታት በአንተ ቤት ነበርሁ፥ ዐሥራ አራት ዓመት ስለ ሁለቱ ሴቶች ልጆችህ፥ ስድስት ዓመትም ስለ በጎችህ ተገዛሁልህ፥ ደመወዜንም ዐሥር ጊዜ ለዋወጥኸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ከአንተ ጋር የነበርኩበትን ኻያ ዓመት ያሳለፍኩት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ከዚህም ዐሥራ አራቱን ዓመት ያገለገልኩህ ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ለማግኘት ብዬ ነው፤ የቀሩትን ስድስት ዓመቶች ያገለገልኩህ መንጋዎችህን ለማግኘት ብዬ ነው። ይህም ሆኖ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ ለዋወጥክብኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 እንዲሁ በአንተ ቤት ሀያ ዓመት ነበርሁ አሥራ አራት ዓመት ስለ ሁለቱ ሴቶች ልጆችህ ስድስት ዓመትም ስለ በጎችህ ተገዛሁልህ፤ ደመወዜንም አሥር ጊዜ ለዋወጥኸው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 31:41
12 交叉引用  

በእ​ር​ሱም ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀ​መጥ። የወ​ን​ድ​ምህ ቍጣ ከአ​ንተ እስ​ኪ​በ​ርድ ድረስ፥


ላባም ያዕ​ቆ​ብን፥ “ወን​ድሜ ስለ​ሆ​ንህ በከ​ንቱ አታ​ገ​ለ​ግ​ለ​ኝም ደመ​ወ​ዝህ ምን​ድን ነው? ንገ​ረኝ” አለው


ደመ​ወ​ዝ​ህን ንገ​ረኝ፤ እር​ሱ​ንም እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለው።


ሃያ አንድ ዓመት በጎ​ች​ህ​ንና ፍየ​ሎ​ች​ህን ስጠ​ብቅ ኖርሁ፥ ከበ​ጎ​ች​ህም ጠቦ​ቶ​ችን አል​በ​ላ​ሁም፤


የቀን ሐሩር፥ የሌ​ሊት ቍር ይበ​ላኝ ነበር፤ ዕን​ቅ​ል​ፍም ከዐ​ይኔ ጠፋ።


እኔ ባለኝ ጕል​በቴ ሁሉ አባ​ታ​ች​ሁን እን​ዳ​ገ​ለ​ገ​ልሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


አባ​ታ​ችሁ ግን አሳ​ዘ​ነኝ፥ ደመ​ወ​ዜ​ንም ዐሥር ጊዜ ለወጠ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ክፉን ያደ​ር​ግ​ብኝ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደ​ለ​ትም።


እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “ለጌ​ታዬ ለዔ​ሳው፦ ባሪ​ያህ ያዕ​ቆብ እን​ዲህ አለ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ በላባ ዘንድ በስ​ደት ተቀ​መ​ጥሁ፤ እስከ ዛሬ ድረስ ቈየሁ፤


ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አሁን እኔ ባለ​ሁ​በት አለሁ፤ ለእ​ኔም የሰ​ጠኝ ጸጋው ለከ​ንቱ የሆ​ነ​ብኝ አይ​ደ​ለም፤ እኔም ከሁሉ ይልቅ ደከ​ምሁ፤ ነገር ግን በእኔ ላይ ያደ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አጸ​ናኝ እንጂ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም።


በመ​ን​ገድ ዘወ​ትር መከራ እቀ​በል ነበር፤ በወ​ን​ዝም መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ ወን​በ​ዴ​ዎ​ችም አሠ​ቃ​ዩኝ፤ ዘመ​ዶ​ችም አስ​ጨ​ነ​ቁኝ፤ አሕ​ዛብ መከራ አጸ​ኑ​ብኝ፤ በከ​ተማ መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ በበ​ረ​ሃም መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ በባ​ሕ​ርም መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ ሐሰ​ተ​ኞች መም​ህ​ራን መከራ አጸ​ኑ​ብኝ።


跟着我们:

广告


广告