Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 31:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በጎቹ በሚ​ፀ​ንሱ ጊዜ ዐይ​ኔን አን​ሥቼ በሕ​ልም አየሁ፤ እነ​ሆም፥ በበ​ጎ​ችና በፍ​የ​ሎች ላይ የሚ​ን​ጠ​ላ​ጠ​ሉት የበ​ጎ​ችና የፍ​የ​ሎች አው​ራ​ዎች ነጭ፥ ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮ​ችና ሐመደ ክቦ ነበሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “እንስሳቱ በሚጠቁበት ወራት፣ የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች መልካቸው፣ ሽመልመሌ፣ ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸው መሆናቸውን ዐይኔን አንሥቼ በሕልሜ አየሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በመንጋዎቹ መራቢያ ወራት ዐይኖቼን አነሳሁ፥ በሕልምም በበጎቹ ላይ የሚንጠላጠሉት አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፥ ዝንጉርጉርና ነቊጣ እንደ ነበሩ አየሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “እንስሶቹ ለመፅነስ ፍትወት በሚያድርባቸው ወራት የሚያጠቁአቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፥ ዝንጒርጒርና ነቊጣ መሆናቸውን በሕልም አየሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እንዲህም ሆነ በጎቹ በጎመጁ ጊዜ ዓይኔን አንሥቼ በሕልም አየሁ እነሆም በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችን የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ነበሩ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 31:10
11 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም አለው፥ “ይህን በል​ብህ ቅን​ነት እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ እኔ ዐወ​ቅሁ፤ እኔም ደግሞ በፊቴ ኀጢ​አ​ትን እን​ዳ​ት​ሠራ ጠበ​ቅ​ሁህ፤ ስለ​ዚ​ህም ትቀ​ር​ባት ዘንድ አል​ተ​ው​ሁ​ህም።


ሕል​ምም አለመ፤ እነ​ሆም መሰ​ላል በም​ድር ላይ ተተ​ክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነ​ሆም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ይወ​ጡ​በ​ትና ይወ​ር​ዱ​በት ነበር።


በጎ​ቹም መጥ​ተው በጠጡ ጊዜ ሽመ​ል​መሌ መሳ​ይና ዝን​ጕ​ር​ጕር፥ ነቍ​ጣም ያለ​በ​ትን በበ​ት​ሮቹ አም​ሳል ፀነሱ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም፦ ‘ያዕ​ቆብ ያዕ​ቆብ’ አለኝ፤ እኔም፦ ‘እነ​ሆኝ ምን​ድን ነው?’ አል​ሁት።


እን​ዲ​ህም አለኝ፦ ዐይ​ን​ህን አቅ​ን​ተህ እይ፤ በበ​ጎ​ችና በፍ​የ​ሎች ላይ የሚ​ን​ጠ​ላ​ጠ​ሉት የበ​ጎ​ችና የፍ​የ​ሎች አው​ራ​ዎች ነጭ፥ ሐመደ ክቦና ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮች ናቸው፤ ላባ በአ​ንተ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን አይ​ቻ​ለ​ሁና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ ሶር​ያ​ዊው ወደ ላባ በሌ​ሊት በሕ​ልም መጥቶ፥ “በባ​ሪ​ያዬ በያ​ዕ​ቆብ ላይ ክፉ ነገር እን​ዳ​ት​ና​ገር ተጠ​ን​ቀቅ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የአ​ባ​ታ​ች​ሁን በጎች ሁሉ ነሥቶ ለእኔ ሰጠኝ።


ዮሴ​ፍም ሕል​ምን አለመ፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ነገ​ራ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በገ​ባ​ዖን ለሰ​ሎ​ሞን በሌ​ሊት በሕ​ልም ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን፥ “እን​ድ​ሰ​ጥህ የም​ት​ፈ​ል​ገ​ውን ለምን” አለው።


እር​ሱም፥ “ቃሌን ስሙ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ የሆነ ቢኖር በራ​እይ እገ​ለ​ጥ​ለ​ታ​ለሁ፤ ወይም በሕ​ልም እና​ገ​ረ​ዋ​ለሁ።


“ከአ​ን​ተም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምል​ክ​ትም፥ ተአ​ም​ራ​ትም ቢሰ​ጥህ፥


跟着我们:

广告


广告