ዘፍጥረት 30:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)43 ያዕቆብም እጅግ ባለጠጋ ሆነ፤ ሴቶችም ወንዶችም አገልጋዮች፥ ብዙ ከብትም፤ ላሞችም፥ በጎችም፥ ግመሎችና አህዮችም ሆኑለት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም43 በዚህም ሁኔታ ይህ ሰው እጅግ ባለጠጋ ሆነ፤ የብዙ መንጎች፣ የሴትና የወንድ አገልጋዮች፣ እንዲሁም የግመሎችና የአህዮች ባለቤት ሆነ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)43 ያ ሰውም እጅግ ባለ ጠጋ ሆነ፥ ብዙም ከብት ሴቶችም ወንዶችም ባርያዎች ግመሎችም አህዮችም ሆኑለት። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም43 በዚህ አኳኋን ያዕቆብ እጅግ ባለ ጸጋ ሆነ፤ ብዙ መንጋዎች፤ ሴቶችና ወንዶች አገልጋዮች፥ ብዙ ግመሎችና አህዮችም ነበሩት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)43 ያ ሰውም እጅግ ባለ ጠጋ ሁነ፤ ብዙም ከብት ሴቶችም ወንዶችም ባሪያዎች ግመሎችም አህዮችም ሆኑለት። 参见章节 |