Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 29:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እነ​ር​ሱም አሉ፥ “እረ​ኞች ሁሉ ካል​ተ​ሰ​በ​ሰ​ቡና ድን​ጋ​ዪ​ቱን ከጕ​ድ​ጓዱ አፍ ካላ​ነ​ሡ​አት በቀር አን​ች​ልም፤ ከዚ​ያም በኋላ በጎ​ቹን እና​ጠ​ጣ​ለን።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እነርሱም፣ “መንጎቹ ሁሉ ተሰብስበው ድንጋዩ ከጕድጓዱ አፍ ካልተንከባለለ በቀር አንችልም፤ ከዚያም በጎቹን እናጠጣቸዋለን” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እነርሱም አሉ፦ “መንጎች ሁሉ እስኪከማቹና ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ እስኪገለብጡት ድረስ አንችልም፥ ከዚያም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እነርሱም “እረኞች ሁሉ መንጋዎቻቸውን ይዘው እዚህ ከመሰብሰባቸው በፊት ምንም ማድረግ አንችልም፤ ሁሉም እዚህ ከመጡ በኋላ ግን ድንጋዩን በኅብረት አንከባለን በጎቹን እናጠጣቸዋለን” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እነርሱም አሉ፦ መንጎች ሁሉ እስኪገለብጡት ድረስ አንችልም ከዚይም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 29:8
8 交叉引用  

መን​ጎ​ችም ሁሉ ከዚያ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ እረ​ኞች ድን​ጋ​ይ​ዋን ከጕ​ድ​ጓዱ አፍ ገለል አድ​ር​ገው በጎ​ቹን ያጠጡ ነበር፤ ድን​ጋ​ይ​ዋ​ንም ወደ ስፍ​ራው መል​ሰው በጕ​ድ​ጓዱ አፍ እን​ደ​ገና ይገ​ጥ​ሙት ነበር።


እር​ሱም፥ “ቀኑ ገና ቀትር ነው፥ ከብ​ቶቹ የሚ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ሰዓ​ቱም ገና አል​ደ​ረ​ሰም፤ አሁ​ንም በጎ​ቹን አጠ​ጡና ሄዳ​ችሁ አሰ​ማ​ሩ​አ​ቸው” አላ​ቸው።


እር​ሱም ገና ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሲነ​ጋ​ገር እነሆ፥ የላባ ልጅ ራሔል የአ​ባ​ት​ዋን በጎች ይዛ ደረ​ሰች፤ እር​ስዋ የአ​ባ​ቷን በጎች ትጠ​ብቅ ነበ​ርና።


የዲና ወን​ድ​ሞች ስም​ዖ​ንና ሌዊም እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “እኅ​ታ​ች​ንን ላል​ተ​ገ​ረዘ ሰው ለመ​ስ​ጠት ይህን ነገር እና​ደ​ርግ ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ንም፤ ይህ ነውር ይሆ​ን​ብ​ና​ልና።


ለእ​ር​ሱም ለብ​ቻው አቀ​ረቡ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ለብ​ቻ​ቸው፤ ከእ​ርሱ ጋር ለሚ​በ​ሉት ለግ​ብፅ ሰዎ​ችም ለብ​ቻ​ቸው፤ የግ​ብፅ ሰዎች ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ጋር መብ​ላት አይ​ች​ሉ​ምና፥ ይህ ለግ​ብፅ ሰዎች እንደ መር​ከስ ነውና።


እርስ በርሳቸውም “ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል?” ይባባሉ ነበር፤


ያቺ​ንም ድን​ጋይ ከመ​ቃ​ብሩ ላይ ተን​ከ​ባ​ልላ አገ​ኙ​አት።


በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ዳገት በወጡ ጊዜ ቈነ​ጃ​ጅት ውኃ ሊቀዱ ሲወጡ አገ​ኙና፥ “ባለ ራእይ በዚህ አለ ወይ?” አሉ​አ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告