Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 29:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ያዕ​ቆ​ብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ይወ​ድ​ዳት ስለ​ነ​በረ በእ​ርሱ ዘንድ ጥቂት ቀን ሆነ​ለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ያዕቆብም ራሔልን ለማግኘት ሲል ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ለርሷ ካለው ፍቅር የተነሣ፣ ሰባት ዓመት እንደ ጥቂት ቀን ሆኖ ታየው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፥ እርሷንም ይወድዳት ስለ ነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ሆነለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ያዕቆብ ራሔልን ለማግባት ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ይሁን እንጂ ራሔልን በጣም ይወዳት ስለ ነበር የቈየበት ጊዜ ጥቂት ቀን ብቻ መስሎ ታየው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ እርስዋንም ይወድዳት ስለነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ሆነለት።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 29:20
14 交叉引用  

ይስ​ሐ​ቅም ወደ እናቱ ቤት ገባ፤ ርብ​ቃ​ንም ወሰ​ዳት፤ ሚስ​ትም ሆነ​ችው፤ ወደ​ዳት፤ ይስ​ሐ​ቅም ስለ እናቱ ስለ ሣራ ተጽ​ናና።


ላባም፥ “ለሌላ ሰው ከም​ሰ​ጣት ይልቅ ለማ​ው​ቅህ ለዘ​መዴ ለአ​ንተ ብሰ​ጣት ይሻ​ላል፤ ከእኔ ጋር ተቀ​መጥ” አለው።


ለዚ​ችም ሰባት ዓመት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለ​ም​ታ​ገ​ለ​ግ​ለኝ አገ​ል​ግ​ሎት እር​ስ​ዋን ደግሞ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”


ያዕ​ቆ​ብም ወደ ራሔል ደግሞ ገባ። ራሔ​ል​ንም ከልያ ይልቅ ወደ​ዳት፤ ሌላ ሰባት ዓመ​ትም ተገ​ዛ​ለት።


ስለ እነ​ርሱ የተ​ገ​ዛ​ሁ​ላ​ቸ​ውን ሚስ​ቶ​ቼ​ንና ልጆ​ችን ስጠ​ኝና ልሂድ፤ የተ​ገ​ዛ​ሁ​ል​ህን መገ​ዛት ታው​ቃ​ለ​ህና።”


እኛ በእ​ርሱ ዘንድ እንደ ባዕድ የተ​ቈ​ጠ​ርን አይ​ደ​ለ​ምን? እርሱ እኛን ሽጦ ዋጋ​ች​ንን በል​ቶ​አ​ልና።


ብላ​ቴ​ና​ውም ይህን ነገር ያደ​ርግ ዘንድ አል​ዘ​ገ​የም፤ የያ​ዕ​ቆ​ብን ልጅ ወድ​ዶ​አ​ልና፤ እር​ሱም ከአ​ባቱ ቤተ ሰብእ ሁሉ የከ​በረ ነበረ።


በገ​ለ​ዓድ ባይ​ሆ​ንም እንኳ በጌ​ል​ጌላ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን የሚ​ሠዉ አለ​ቆች ስተ​ዋል፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም በእ​ርሻ ትልም ላይ እንደ አለ የድ​ን​ጋይ ክምር ነው።


ያዕ​ቆብ ወደ ሶርያ ሀገር ሸሸ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ስለ ሚስት አገ​ለ​ገለ፤ ስለ ሚስ​ትም ጠበቀ።


በሁሉ ያቻ​ች​ላል፤ በሁ​ሉም ያስ​ተ​ማ​ም​ናል፤ በሁ​ሉም ተስፋ ያስ​ደ​ር​ጋል፥ በሁ​ሉም ያስ​ታ​ግ​ሣል።


የክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር በዚህ አሳብ እን​ድ​ን​ጸና ያስ​ገ​ድ​ደ​ናል፤ ሁሉ ፈጽ​መው ስለ ሞቱ አንዱ ስለ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞቶ​አ​ልና።


ክር​ስ​ቶስ እንደ ወደ​ዳ​ችሁ፥ ራሱ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ የሚ​ሆን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ቍር​ባን አድ​ርጎ እንደ ሰጠ​ላ​ችሁ በፍ​ቅር ተመ​ላ​ለሱ።


የሳ​ኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖች ይህን ቃል በዳ​ዊት ጆሮ ተና​ገሩ፤ ዳዊ​ትም፥ “እኔ የተ​ዋ​ረ​ድ​ሁና ክብር የሌ​ለኝ ሰው ስሆን ለን​ጉሥ አማች እሆን ዘንድ ለእ​ና​ንተ ትንሽ ነገር ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልን?” አለ።


跟着我们:

广告


广告