Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 28:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ይስ​ሐ​ቅም ልጁ ያዕ​ቆ​ብን ላከው፤ እር​ሱም የያ​ዕ​ቆ​ብና የዔ​ሳው እናት የር​ብቃ ወን​ድም የሚ​ሆን የሶ​ር​ያ​ዊው ባቱ​ኤል ልጅ ላባ ወዳ​ለ​በት ወደ ሁለቱ ወን​ዞች መካ​ከል ሄደ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ይሥሐቅም ያዕቆብን በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ወደሚኖረው፣ የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም ወደ ሆነው ወደ ሶርያዊው የባቱኤል ልጅ ወደ ላባ ላከው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ይስሐቅም ያዕቆብን ላከው፥ እርሱም የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም የሚሆን የሶርያዊ ባቱኤል ልጅ ላባ ወዳለበት ወደ ሁለቱ ወንዞች መካከል ሄደ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በዚህ ሁኔታ ይስሐቅ ያዕቆብን አሰናበተው፤ ያዕቆብም በመስጴጦምያ ወደሚኖረው ወደ ላባ ሄደ፤ ላባ የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም ነበረ፤ አባቱም ሶርያዊው ባቱኤል ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ይስሐቅም ያዕቆብን ሰደደው እርሱም የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም የሚሆን የሶርያዊ ባቱኤል ልጅ ላባ ወዳለበት ወደ ሁለቱ ወንዞች መካከል ሄደ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 28:5
12 交叉引用  

ባቱ​ኤ​ልም ርብ​ቃን ወለደ፤ ሚልካ ለአ​ብ​ር​ሃም ወን​ድም ለና​ኮር የወ​ለ​ደ​ች​ለት ስም​ንቱ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።


ከዚ​ህም ሁሉ በኋላ እርሱ፥ ከእ​ርሱ ጋር ያሉ​ትም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም አደሩ፤ በማ​ለ​ዳም ተነ​ሥቶ፥ “ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ቱኝ” አላ​ቸው።


ይስ​ሐ​ቅም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ የሶ​ር​ያ​ዊ​ውን የላ​ባን እኅት፥ የሶ​ር​ያ​ዊ​ውን የባ​ቱ​ኤ​ልን ልጅ ርብ​ቃን ከሁ​ለቱ ከሶ​ርያ ወን​ዞች መካ​ከል በወ​ሰ​ዳት ጊዜ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር።


አሁ​ንም ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ስማ፤ ተነ​ሣና በሶ​ርያ ወን​ዞች መካ​ከል ወደ ካራን ምድር ወደ ወን​ድሜ ወደ ላባ ሂድ፤


ተነ​ሣና ወደ እና​ትህ አባት ወደ ባቱ​ኤል ቤት ወደ ሁለቱ ወን​ዞች መካ​ከል ሂድ፤ ከዚ​ያም ከእ​ና​ትህ ከር​ብቃ ወን​ድም ከላባ ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን አግባ።


ያዕ​ቆ​ብም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ የያ​ዕ​ቆ​ብና የዔ​ሳው እናት የር​ብቃ ወን​ድም የሶ​ርያ ሰው የባ​ቱ​ኤል ልጅ ወደ​ሚ​ሆን ወደ ላባ ሄደ።


ያዕ​ቆ​ብም የአ​ባቷ ዘመ​ድና የር​ብቃ ልጅ መሆ​ኑን ለራ​ሔል አስ​ታ​ወ​ቃት፤ እር​ስ​ዋም ሮጣ ሄዳ ለአ​ባቷ ይህን ነገር ነገ​ረ​ችው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ ሶር​ያ​ዊው ወደ ላባ በሌ​ሊት በሕ​ልም መጥቶ፥ “በባ​ሪ​ያዬ በያ​ዕ​ቆብ ላይ ክፉ ነገር እን​ዳ​ት​ና​ገር ተጠ​ን​ቀቅ” አለው።


ያዕ​ቆ​ብም ወደ አባቱ ወደ ይስ​ሐቅ፥ አብ​ር​ሃ​ምና ይስ​ሐቅ እን​ግ​ዶች ሆነው ወደ ተቀ​መ​ጡ​ባት በአ​ር​ባቅ ከተማ ወደ​ም​ት​ገ​ኘው ወደ መምሬ እር​ስ​ዋም ኬብ​ሮን ወደ​ም​ት​ባ​ለው መጣ።


የሶ​ር​ያም ሰዎች ከገ​ን​ዘ​ብሽ ብዛት የተ​ነሣ ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፥ ከአ​ን​ቺም ጋር አንድ ከሆኑ ከብዙ ሰዎች ጋር ትነ​ግጂ ነበር፤ ነጭ ሐር​ንና ዕን​ቍን፥ ቀይ ሐር​ንና ወርቀ ዘቦን ከር​ከ​ዴን የሚ​ባል ዕን​ቍ​ንና ልባ​ን​ጃም የሚ​ባል ሽቱን ከተ​ር​ሴስ ያመ​ጡ​ልሽ ነበር፤ ገበ​ያ​ሽ​ንም ረዓ​ሙ​ትና ቆር​ኮር መሉት።


በገ​ለ​ዓድ ባይ​ሆ​ንም እንኳ በጌ​ል​ጌላ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን የሚ​ሠዉ አለ​ቆች ስተ​ዋል፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም በእ​ርሻ ትልም ላይ እንደ አለ የድ​ን​ጋይ ክምር ነው።


በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፦ አባቴ ከሶ​ርያ ወጥቶ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚ​ያም በቍ​ጥር ጥቂት ሆኖ ኖረ፤ በዚ​ያም ታላ​ቅና የበ​ረታ፥ ብዙም ሕዝብ ሆነ።


跟着我们:

广告


广告