Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 28:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ያዕ​ቆ​ብም ማልዶ ተነሣ፤ ተን​ተ​ር​ሷት የነ​በ​ረ​ች​ው​ንም ድን​ጋይ ወስዶ ሐው​ልት አድ​ርጎ አቆ​ማት፥ በላ​ይ​ዋም ዘይ​ትን አፈ​ሰ​ሰ​ባት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ያዕቆብም በማግስቱም ማልዶ ተነሣ፣ ተንተርሶት ያደረውን ድንጋይ አንሥቶ እንደ ሐውልት አቆመው፤ በዐናቱም ላይ የወይራ ዘይት አፈሰሰበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ያዕቆብም ማልዶ ተነሣ፥ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፥ በላዩም ዘይትን አፈሰሰበት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ያዕቆብ በማግሥቱ ጠዋት በማለዳ ተነሣ፤ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ መታሰቢያ እንዲሆን እንደ ሐውልት አቆመው፤ በላዩ ላይም የወይራ ዘይት አፈሰሰበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ያዕቆብም ማልዶ ተነሣ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፥ በላዩም ዘይትን አፈሰሰበት።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 28:18
16 交叉引用  

አብ​ር​ሃ​ምም ማልዶ ተነሣ፤ እን​ጀ​ራ​ንም ወሰደ፤ የውኃ አቍ​ማ​ዳ​ንም ለአ​ጋር በት​ከ​ሻዋ አሸ​ከ​ማት፤ ሕፃ​ኑ​ንም ሰጥቶ አስ​ወ​ጣት፤ እር​ስ​ዋም ሄደች፤ በዐ​ዘ​ቅተ መሐ​ላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅ​በ​ዘ​በ​ዘች።


አብ​ር​ሃ​ምም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ሁለ​ቱ​ንም ሎሌ​ዎ​ቹ​ንና ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ሰነ​ጠቀ፤ ተነ​ሥ​ቶም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለው ቦታ ሄደ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ደረሰ።


ወደ አንድ ስፍ​ራም ደረሰ፤ ፀሐ​ይም ጠልቃ ነበ​ርና በዚያ አደረ፤ ከዚ​ያም ስፍራ ድን​ጋ​ዮች አንድ ድን​ጋይ አነሣ፤ ከራ​ሱም በታች ተን​ተ​ርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ።


ሐው​ል​ቱን ዘይት በቀ​ባ​ህ​ባት፥ በዚ​ያች ለእኔ ስእ​ለት በተ​ሳ​ል​ህ​ባት ሀገር የተ​ገ​ለ​ጥ​ሁ​ልህ ፈጣ​ሪህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ። አሁ​ንም ተነ​ሥ​ተህ ከዚህ ሀገር ውጣ፤ ወደ ተወ​ለ​ድ​ህ​ባ​ትም ምድር ተመ​ለስ፤ እኔም ከአ​ንተ ጋር እኖ​ራ​ለሁ።”


ያዕ​ቆ​ብም ድን​ጋይ ወስዶ ሐው​ልት አቆመ።


ያዕ​ቆ​ብም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር በተ​ነ​ጋ​ገ​ረ​በት ቦታ የድ​ን​ጋይ ሐው​ልት ተከለ፤ የመ​ጠጥ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም በእ​ርሱ ላይ አፈ​ሰሰ፤ ዘይ​ት​ንም አፈ​ሰ​ሰ​በት።


ያዕ​ቆ​ብም በመ​ቃ​ብ​ርዋ ላይ ሐው​ልት አቆመ፤ እር​ስ​ዋም እስከ ዛሬ የራ​ሔል የመ​ቃ​ብ​ርዋ ሐው​ልት ትባ​ላ​ለች።


አቤ​ሴ​ሎ​ምም በሕ​ይ​ወቱ ሳለ፥ “ለስሜ መታ​ሰ​ቢያ የሚ​ሆን ልጅ የለ​ኝም” ብሎ ሐው​ልት ወስዶ በን​ጉሥ ሸለቆ ውስጥ ለራሱ በስሙ አቁሞ ነበር፤ ያችም ሐው​ልት እስከ ዛሬ ድረስ “እደ አቤ​ሴ​ሎም” ተብላ ትጠ​ራ​ለች።


አንተ በም​ት​ሄ​ድ​በት በሲ​ኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕው​ቀ​ትና ጥበብ አይ​ገ​ኙ​ምና እጅህ ለማ​ድ​ረግ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ እንደ ኀይ​ልህ አድ​ርግ።


በዚያ ቀን በግ​ብፅ ምድር መካ​ከል አን​ዲቱ ከተማ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ትሆ​ና​ለች፤ በዳ​ር​ቻ​ዋም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ዐ​ምድ ይሆ​ናል።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ ድን​ኳ​ኑን ፈጽሞ በተ​ከ​ለ​ባት፥ እር​ስ​ዋ​ንና ዕቃ​ዋን ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት፥ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንና ዕቃ​ው​ንም ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት ቀን፥


ኢያ​ሱም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግ​ሮች በቆ​ሙ​በት ስፍራ በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።


ሳሙ​ኤ​ልም አንድ ድን​ጋይ ወስዶ በመ​ሴ​ፋና በአ​ሮ​ጌው ከተማ መካ​ከል አኖ​ረው፤ ስሙ​ንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረድ​ቶ​ናል” ሲል “አቤ​ን​ኤ​ዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድ​ኤት ማለት ነው።


跟着我们:

广告


广告