Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 27:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ዔሳ​ውም አለ፥ “በእ​ው​ነት ስሙ ያዕ​ቆብ ተባለ፤ ሁለት ጊዜ አሰ​ና​ክ​ሎ​ኛ​ልና፤ መጀ​መ​ሪያ ብኵ​ር​ና​ዬን ወሰደ፤ አሁ​ንም እነሆ በረ​ከ​ቴን ወሰደ።” ዔሳ​ውም አባ​ቱን አለው፥ “ደግ​ሞም አባቴ ሆይ፥ ለእኔ በረ​ከ​ትን አላ​ስ​ቀ​ረ​ህ​ል​ኝ​ምን?”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ዔሳውም፣ “ይህ ሰው ያዕቆብ መባሉ ትክክል አይደለምን? እኔን ሲያታልለኝ ይህ ሁለተኛ ጊዜው ነው፤ መጀመሪያ ብኵርናዬን ወሰደብኝ፤ አሁን ደግሞ ምርቃቴን ቀማኝ” አለ። ቀጥሎም፣ “ታዲያ ለእኔ ያስቀረኸው ምንም ምርቃት የለም?” ብሎ ጠየቀ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 እርሱም እንዲህ አለ፦ “በእውነት ስሙ ያዕቆብ ተባለ፥ ሁለት ጊዜ አሰናክሎኛልና፥ ብኩርናዬን ወሰደ፥ አሁንም እነሆ በረከቴን ወሰደ። ደግሞም፦ ለእኔ በረከትን አላስቀረህልኝምን?” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ዔሳውም “እርሱ እኔን ሲያሰናክለኝ ይህ ሁለተኛው ነው፤ ያዕቆብ መባሉ ተገቢ ነው፤ ከዚህ በፊት ብኲርናዬን ወሰደብኝ፤ አሁን ደግሞ ምርቃቴን ቀማኝ፤ ታዲያ፥ ለእኔ ያስቀረኸው ምንም ምርቃት የለምን?” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 እርሱም አለ፦ በእውነት ስሙ ያዕቆብ ተባለ ሁለት ጊዜ አሰናክሎኛልና፤ ብኵርናዬን ወሰደ አሁንም እነሆ በረከቴን ወሰደ። ደግሞም፦ ለእኔ በረከትን አላስቀረህልኝምን? አለ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 27:36
4 交叉引用  

ከዚ​ያም በኋላ ወን​ድሙ ወጣ፤ በእ​ጁም የዔ​ሳ​ውን ተረ​ከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙ​ንም ያዕ​ቆብ ብላ ጠራ​ችው። ርብቃ ዔሳ​ው​ንና ያዕ​ቆ​ብን በወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው ጊዜ ይስ​ሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር።


አለ​ውም፥ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ስምህ እስ​ራ​ኤል ይባል እንጂ ያዕ​ቆብ አይ​ባል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ከሰው ጋር ታግ​ለህ በር​ት​ተ​ሃ​ልና።”


ናት​ና​ኤ​ልም፥ “በውኑ ከና​ዝ​ሬት ደግ ሰው ሊወጣ ይቻ​ላ​ልን?” አለው፤ ፊል​ጶ​ስም፥ “መጥ​ተህ እይ” አለው።


跟着我们:

广告


广告