Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 26:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ዔሳ​ውም አርባ ዓመት ሲሆ​ነው የኬ​ጢ​ያ​ዊው የብ​ኤ​ልን ልጅ ዮዲ​ትን፥ የኬ​ጢ​ያ​ዊው የኤ​ሎ​ንን ልጅ ቤሴ​ሞ​ት​ንም ሚስ​ቶች አድ​ርጎ አገባ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ዔሳው አርባ ዓመት በሆነው ጊዜ፣ የኬጢያዊውን የብኤሪን ልጅ ዮዲትን እንዲሁም የኬጢያዊውን የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትን አገባ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የሒታውያዊ የብኤሪን ልጅ ዮዲትን፥ የሒታውያዊ የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ዔሳው አርባ ዓመት ሲሆነው የብኤሪን ልጅ ዮዲትንና የኤሎንን ልጅ ባሴማትን አገባ፤ ሁለቱም ሒታውያን ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊ የብኤሪን ልጅ ዮዲትን የኬጢያዊ የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ

参见章节 复制




ዘፍጥረት 26:34
11 交叉引用  

“እጅ​ህን በእጄ ላይ አድ​ርግ፤ እኔም አብሬ ከም​ኖ​ራ​ቸው ከከ​ነ​ዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይ​ስ​ሐቅ ሚስት እን​ዳ​ት​ወ​ስ​ድ​ለት በሰ​ማ​ይና በም​ድር አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ል​ሃ​ለሁ፤


ርብ​ቃም ይስ​ሐ​ቅን አለ​ችው፥ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተ​ነሣ ሕይ​ወ​ቴን ጠላ​ሁት፤ ያዕ​ቆብ ከዚህ ሀገር ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን የሚ​ያ​ገባ ከሆነ በሕ​ይ​ወት መኖር ለእኔ ምኔ ነው?”


የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ሴቶች ልጆች በአ​ባቱ በይ​ስ​ሐቅ ፊት የተ​ጠሉ እንደ ሆኑ ዔሳው በአየ ጊዜ፥


ዔሳው ወደ ይስ​ማ​ኤል ሄደ፤ ቤሴ​ሞ​ት​ንም በፊት ካሉ ሚስ​ቶቹ ጋር ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ወሰ​ዳት፤ እር​ስ​ዋም የና​ኮር ወን​ድም የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ የሆ​ነው የይ​ስ​ማ​ኤል ልጅና የና​ቡ​ዓት እኅት ናት።


የዔ​ሳው ልጅ የራ​ጉ​ኤል ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ናሖት፥ ዛራ፥ ሲም፥ ሞዛህ፤ እነ​ዚ​ህም የዔ​ሳው ሚስት የቤ​ሴ​ሞት ልጆች ናቸው።


ዔሳው ከከ​ነ​ዓን ልጆች ሚስ​ቶ​ችን አገባ፤ የኬ​ጤ​ያ​ዊ​ውን የዔ​ሎን ልጅ ሐዳ​ሶን፥ የኤ​ው​ያ​ዊው የሴ​ቤሶ ልጅ ሐና የወ​ለ​ዳ​ትን ኤሌ​ባ​ማን፥


ኤሌ​ባ​ማም ዮሔ​ልን፥ ይጉ​ሜ​ልን፥ ቆሬ​ንም ወለ​ደች። በከ​ነ​ዓን ምድር የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት የዔ​ሳው ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።


ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ም​ንም ከወ​ንድ ልጆ​ችህ፥ ሴቶች ልጆ​ች​ህ​ንም ከወ​ንድ ልጆ​ቻ​ቸው ጋር እን​ዳ​ታ​ጋባ፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለው ሲያ​መ​ነ​ዝሩ ከአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው በኋላ ሄደው አመ​ን​ዝ​ረ​ውም ልጆ​ች​ህን እን​ዳ​ያ​ስቱ ተጠ​ን​ቀቅ።


ነገር ግን እን​ዳ​ት​ሴ​ስኑ ሰው ሁሉ በሚ​ስቱ ይወ​ሰን፤ ሴትም ሁላ በባ​ልዋ ትወ​ሰን።


ለጥ​ቂት መብል ብኵ​ር​ና​ውን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ሴሰ​ኛና ርኩስ የሚ​ሆን አይ​ኑር።


ዳዊ​ትም ኬጤ​ያ​ዊ​ዉን አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንና የሶ​ር​ህ​ያን ልጅ የኢ​ዮ​አ​ብን ወን​ድም አቢ​ሳን፥ “ወደ ሳኦል ወደ ሰፈሩ ከእኔ ጋር የሚ​ገባ ማን ነው?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው፤ አቢ​ሳም፥ “እኔ ከአ​ንተ ጋር እገ​ባ​ለሁ” አለ።


跟着我们:

广告


广告