Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 26:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ከዚ​ያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድ​ጓድ ቈፈረ፤ ስለ እር​ስ​ዋም አል​ተ​ጣ​ሉ​ትም፤ ስም​ዋ​ንም “መር​ኅብ” ብሎ ጠራት፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሰ​ፋ​ልን፤ በም​ድ​ርም አበ​ዛን።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ይሥሐቅም ያን ቦታ ትቶ ሌላ ስፍራ ላይ የውሃ ጕድጓድ አስቈፈረ፤ በዚህ ጊዜ ግን አንድም ሰው ጠብ አላነሣበትም፤ ስለዚህ ያን የውሃ ጕድጓድ፣ “አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጥቶናል፤ እኛም በምድር ላይ እንበዛለን” ሲል ርኆቦት ብሎ ጠራው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጉድጓድ አስቈፈረ፥ ስለ እርሷም አልተጣሉም፥ ስምዋንም “ርኆቦት” ብሎ ጠራት እንዲህ ሲል፦ “አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፥ በምድርም እንበዛለን።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ የውሃ ጒድጓድ ቈፈረ፤ በዚህኛው የውሃ ጒድጓድ ምክንያት ምንም ጠብ ስላልተነሣ “እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጠን፤ በምድር ላይም እንበዛለን ሲል፥ ያንን ቦታ ‘ረሖቦት’ ” ብሎ ሰየመው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድጓድ አስቋፈረ ስለ እርስዋም አልተጣሉም፤ ስምዋንም፥ ርኖቦት ብሎ ጠራት እንዲህ ሲል፦ አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን በምድርም እንበዛለን።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 26:22
11 交叉引用  

እጅ​ግም በጣም አበ​ዛ​ሃ​ለሁ፤ ሕዝ​ብም፥ ነገ​ሥ​ታ​ትም ከአ​ንተ እን​ዲ​ወጡ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።


ይስ​ሐ​ቅም ከዚያ ሄደ በዚ​ያም ሌላ ጕድ​ጓድ ማሰ፥ ስለ እር​ስ​ዋም ደግሞ ተጣ​ሉት፤ ስም​ዋ​ንም “ጽልእ” ብሎ ጠራት።


አም​ላኬ ከአ​ንተ ጋር ይሂድ፤ ከፍ ከፍም ያድ​ር​ግህ፤ ይባ​ር​ክህ፤ ያብ​ዛህ፤ ብዙ ሕዝ​ብም ሁን ፤


የሁ​ለ​ተ​ኛ​ው​ንም ስም ኤፍ​ሬም ብሎ ጠራው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ከ​ራዬ ሀገር አብ​ዝ​ቶ​ኛ​ልና።”


ሥር​ዐ​ት​ህን እጠ​ብቅ ዘንድ የሚ​ቀ​ናስ ከሆነ መን​ገዴ ይቅና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በጠ​ራ​ሁት ጊዜ ጽድ​ቄን ሰማኝ፥ ከጭ​ን​ቀ​ቴም አሰ​ፋ​ልኝ፤ ይቅር አለኝ፥ ጸሎ​ቴ​ንም ሰማኝ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዙ፤ ተባ​ዙም፤ የተ​ጠ​ሉም ሆኑ። እጅ​ግም ጸኑ፤ ምድ​ሪ​ቱም በእ​ነ​ርሱ ሞላች።


የድ​ን​ኳ​ን​ሽን ስፍራ አስፊ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ች​ሽ​ንም ዘርጊ፤ አት​ቈ​ጥቢ፤ አው​ታ​ሮ​ች​ሽን አስ​ረ​ዝሚ፤ ካስ​ሞ​ች​ሽ​ንም ትከዪ።


እንደ ገና​ም​በ​ቀ​ኝና በግራ ተስ​ፋፊ፤ ዘርሽ አሕ​ዛ​ብን ይወ​ር​ሳ​ሉና፥ የፈ​ረ​ሱ​ት​ንም ከተ​ሞች መኖ​ሪያ ታደ​ር​ጊ​ያ​ለ​ሽና።


跟着我们:

广告


广告