Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 25:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ልጆ​ች​ዋም በሆ​ድዋ ውስጥ ይን​ቀ​ሳ​ቀሱ ነበር ፤ እር​ስ​ዋም፥ “እን​ዲህ እሆን ዘንድ ካለኝ ይህ ለእኔ ምኔ ነው?” አለች። ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትለ​ምን ዘንድ ሄደች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ልጆቹም በማሕፀኗ ውስጥ እርስ በርሳቸው ይጋፉ ጀመር፤ እርሷም “ለምን እንዲህ ይሆንብኛል?” ብላ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሄደች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ልጆቹም በማሕፀንዋ ውስጥ ይገፋፉ ነበር፤ እርሷም፥ “እንዲህ እሆን ዘንድ ከሆነ፥ ስለምንድን ነው የምኖረው?” አለች። ከጌታም ምላሽ ታገኝ ዘንድ ሄደች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የተፀነሱትም መንትያዎች ስለ ነበሩ እርስ በርሳቸው በማሕፀንዋ ውስጥ ይገፋፉ ነበር፤ እርስዋም “ይህን ዐይነት ነገር ለምን ደረሰብኝ?” በማለት ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ ተነሣሣች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ልጆችም በሆድዋ ውስጥ ይገፋፋ ነበር፤ እርስዋም፦ እንዲህ ከሆነ ይህ ለእኔም ምኔ ነው? አለች። ከእግዚአብሔርም ትጠይቅ ዘንድ ሄደች።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 25:22
7 交叉引用  

ቍር​ባ​ና​ች​ሁን በአ​ቀ​ረ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም በእ​ሳት ባሳ​ለ​ፋ​ችሁ ጊዜ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በዐ​ሳ​ባ​ችሁ ሁሉ ረከ​ሳ​ችሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እኔስ እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለ​ሁን? እኔ ሕያው ነኝ! አል​መ​ል​ስ​ላ​ች​ሁም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ​ዚህ ደግሞ አደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ይሹ​ኛል፤ ሰው​ንም እንደ መንጋ አበ​ዛ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ሳሙ​ኤ​ልም፦ ያ ሰው እዚህ ይመጣ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እነሆ፥ በዕቃ መካ​ከል ተሸ​ሽ​ጎ​አል” ብሎ መለሰ።


በውኑ ስለ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ይቅ ዘንድ ዛሬ ጀመ​ር​ሁን? ይህ ከእኔ ይራቅ፤ እኔ ባሪ​ያህ ይህን ሁሉ ትልቅ ወይም ጥቂት ቢሆን አላ​ው​ቅ​ምና ንጉሡ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ነገር በእኔ በባ​ሪ​ያ​ውና በአ​ባቴ ቤት ሁሉ ላይ አያ​ኑር” አለ።


ሳኦ​ልም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም አላ​ሚ​ዎች፥ ወይም በነ​ጋ​ሪ​ዎች፥ ወይም በነ​ቢ​ያት አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም።


ዳዊ​ትም፥ “የእ​ነ​ዚ​ህን ሠራ​ዊት ፍለጋ ልከ​ተ​ልን? አገ​ኛ​ቸ​ዋ​ለ​ሁን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እር​ሱም፥ “ታገ​ኛ​ቸ​ዋ​ለ​ህና፥ ፈጽ​መ​ህም ምር​ኮ​ኞ​ቹን ታድ​ና​ለ​ህና ፍለ​ጋ​ቸ​ውን ተከ​ተል” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ቀድሞ ነቢ​ዩን ባለ ራእይ ይሉት ነበ​ርና አስ​ቀ​ድሞ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ጠ​የቅ ሲሄድ፦ ኑ፤ ወደ ባለ ራእይ እን​ሂድ ይል ነበር።”


跟着我们:

广告


广告