Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 24:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ሰው​ዬ​ውም ወደ ቤት ገባ፤ ግመ​ሎ​ቹ​ንም አራ​ገፈ፤ ለግ​መ​ሎ​ቹም ሣርና ገለባ አቀ​ረ​ቡ​ላ​ቸው፤ እግ​ሩን ይታ​ጠብ ዘንድ ውኃ አመ​ጡ​ለት፤ ከእ​ርሱ ጋር ላሉ ሰዎ​ችም አመ​ጡ​ላ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ሰውየው ከላባ ጋራ ወደ ቤት ሄደ፤ የግመሎቹ ጭነት ተራግፎ ገለባና ድርቈሽ ተሰጣቸው፤ ለርሱና ዐብረውት ለነበሩት ሰዎች የእግር ውሃ ቀረበላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ሰውዬውም ወደ ቤት ገባ፥ ግመሎቹንም አራገፈ፥ ገለባና ገፈራም ለግመሎቹ አቀረበ፥ እግሩን ይታጠብ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ላሉት ሰዎች እግር ውኃ አቀረበ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ከዚህ በኋላ ሰውየው ወደ ቤት ሄደ፤ ላባም በግመሎቹ ላይ የነበረውን ጭነት አራግፎ ገለባና ድርቆሽ አቀረበላቸው፤ ቀጥሎም የአብርሃም አገልጋይና አብረውት የነበሩት ሰዎች እግራቸውን የሚታጠቡበት ውሃ አመጣላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ሰውዮውም ወደ ቤት ገባ ግመሎቹንም አራገፈ ገለባና ገፈራም ለግመሎቹ አቀረበ፤ እግሩን ይታጠብ ዘንድ ከእርሱም ጋር ላሉት ሰዎች እግር ውኃ አቀረበ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 24:32
10 交叉引用  

ውኃ እና​ም​ጣ​ላ​ችሁ፤ እግ​ራ​ች​ሁ​ንም እን​ጠ​ባ​ችሁ።


አላ​ቸ​ውም፥ “ጌቶች ሆይ፥ ወደ ባሪ​ያ​ችሁ ቤት ገብ​ታ​ችሁ እደሩ፤ እግ​ራ​ች​ሁ​ንም ታጠቡ፤ ነገም ማል​ዳ​ችሁ መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “በአ​ደ​ባ​ባዩ እና​ድ​ራ​ለን እንጂ፥ አይ​ሆ​ንም” አሉት።


ይበ​ላም ዘንድ እን​ጀ​ራን አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ እርሱ ግን “ነገ​ሬን እስ​ክ​ና​ገር ደረስ አል​በ​ላም” አለ። እነ​ር​ሱም “ተና​ገር” አሉት።


ላባም የእ​ኅ​ቱን የር​ብ​ቃን ልጅ የያ​ዕ​ቆ​ብን ስም በሰማ ጊዜ ሊቀ​በ​ለው ሮጠ፥ አቅ​ፎም ሳመው፥ ወደ ቤቱም አገ​ባው። ነገ​ሩ​ንም ሁሉ ለላባ ነገ​ረው።


ስም​ዖ​ን​ንም ወደ እነ​ርሱ አወ​ጣ​ላ​ቸው። እግ​ራ​ቸ​ው​ንም ሊታ​ጠቡ ውኃ አመ​ጣ​ላ​ቸው፤ ለአ​ህ​ዮ​ቻ​ቸ​ውም ገፈራ ሰጣ​ቸው።


ወደ ሴቲ​ቱም ዘወር ብሎ ስም​ዖ​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ይህ​ቺን ሴት ታያ​ታ​ለ​ህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ለእ​ግ​ሮች ውኃ ስንኳ አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን አል​ቅሳ በእ​ን​ባዋ እግ​ሬን አራ​ሰች፤ በጠ​ጕ​ር​ዋም አበ​ሰች።


ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።


ወደ ቤቱም አስ​ገ​ባው፤ ለአ​ህ​ዮ​ቹም ገፈራ ጣለ​ላ​ቸው፤ እግ​ራ​ቸ​ው​ንም ታጠቡ፤ በሉም፤ ጠጡም።


ተነ​ሥ​ታም በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ወድቃ ሰገ​ደ​ችና፥ “እነሆ፥ እኔ ገረ​ድህ የጌ​ታ​ዬን ሎሌ​ዎች እግር አጥብ ዘንድ አገ​ል​ጋይ ነኝ” አለች።


跟着我们:

广告


广告