ዘፍጥረት 24:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 ጉትቻውንና አምባሮቹን በእኅቱ እጅ ባየ ጊዜ፥ የእኅቱንም የርብቃን ነገር፦ ያ ሰው እንዲህ አለኝ ያለችውን በሰማ ጊዜ፥ እርሱ ወደዚያ ሰው መጣ፤ እነሆም በውኃው ጕድጓድ አጠገብ ከግመሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም30 እኅቱ ያደረገችውን የወርቅ ቀለበትና አምባሮች እንዳየ፣ እንዲሁም ርብቃ ሰውየው ያላትን ስትናገር እንደ ሰማ፣ ወዲያውኑ ወደ ሰውየው ሄደ፤ በምንጩም ዳር ከግመሎቹ አጠገብ ቆሞ አገኘው፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 ቀለበቱንና አምባሮቹን በእኅቱ እጅ ባየ ጊዜ፥ የእኅቱን የርብቃንም ነገር፦ “ያ ሰው እንዲህ አለኝ” ያለችውን በሰማ ጊዜ፥ እርሱ ወደዚያ ሰው መጣ፥ እነሆም፥ በውኃው ምንጭ አጠገብ ከግመሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 ላባ ወደ ሰውየው የሄደው እኅቱ በጆሮዋ ላይ ያደረገችውን ጒትቻና በእጆችዋ ላይ ያደረገቻቸውን አንባሮች ስላየና ርብቃ ሰውየው ያላትን ስትናገር ስለ ሰማም ነው። እርሱንም በውሃው ጒድጓድ አጠገብ ከግመሎቹ ጋር ቆሞ አገኘው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 ቀለበቱንን አምባሮቹን በእኅቱ እጅ ባየ ጊዜ የእኅቱን የርብቃንም ነገር፦ ያ ሰው እንዲህ አለኝ ያለችውን በሰማ ጊዜ እርሱ ወደዚያ ሰው መጣ እነሆም በውኃው ምንጭ አጠገብ ከግመሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር። 参见章节 |