Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 22:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አብ​ር​ሃ​ምም ዛሬ በዚህ ተራራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጽሞ ታየኝ ሲል ያን ቦታ “ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ብሎ ጠራው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከዚህም የተነሣ አብርሃም የዚያን ስፍራ ስም፣ “እግዚአብሔር ያዘጋጃል” ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም ድረስ፣ “በእግዚአብሔር ተራራ ላይ ይዘጋጃል” ይባላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ስለዚህም አብርሃም ያንን ቦታ “ጌታ ያዘጋጃል (ያህዌ ይርኤ)” ብሎ ሰየመው፤ ዛሬም ቢሆን ሰዎች “ጌታ በተራራው ላይ ያዘጋጃል” ይላሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አብርሃም ያንን ቦታ “እግዚአብሔር ያዘጋጃል” ብሎ ሰየመው፤ ዛሬም ቢሆን ሰዎች “እግዚአብሔር በተራራው ላይ ያዘጋጃል” ይላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አብርሃምም ያንን ቦታ ያህዌ ይርኤ ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም፤ እስከ ዛሬም ድረስ በእግዚአብሔር ተራራ ይታያል ይባላል።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 22:14
19 交叉引用  

አብ​ር​ሃ​ምም ዐይ​ኖ​ቹን አቅ​ንቶ በተ​መ​ለ​ከተ ጊዜ፥ በኋ​ላው እነሆ፥ አንድ በግ ቀን​ዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ሄዶ በጉን ወሰ​ደው፤ በልጁ በይ​ስ​ሐቅ ፈን​ታም ሠዋው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን ከሰ​ማይ ሁለ​ተኛ ጊዜ ጠራው፤ እን​ዲ​ህም አለው፦


አብ​ር​ሃ​ምም፥ “ልጄ ሆይ፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን በግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ጋ​ጃል” አለው፤ ሁለ​ቱም አብ​ረው ሄዱ።


ያዕ​ቆ​ብም ያን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው፤ አስ​ቀ​ድሞ ግን የዚያ ከተማ ስም ሎዛ ነበረ።


በዚ​ያም ስፍራ ባረ​ከው። ያዕ​ቆ​ብም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰው​ነ​ቴም ዳነች” ሲል የዚ​ያን ቦታ ስም “ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ብሎ ጠራው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ኤል​ያስ መጣ እን​ዲ​ህም አለው፦


ሙሴም መሠ​ዊያ ሠራ፤ ስሙ​ንም “ምም​ሕ​ፃን” ብሎ ጠራው፤


ዙሪ​ያ​ዋም ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ክንድ ይሆ​ናል፥ ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ስም፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ አለ’ ተብሎ ይጠ​ራል።”


የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጠሽ ውለጂ፥ አሁን ከከተማ ትወጫለሽና፥ በሜዳም ትቀመጫለሽ፥ ወደ ባቢሎንም ትደርሻለሽ፥ በዚያም ያድንሻል፥ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።


ያም ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእ​ኛም አደረ፤ ለአ​ባቱ አንድ እንደ ሆነ ልጅ ክብር ያለ ክብ​ሩን አየን፤ ጸጋ​ንና እው​ነ​ትን የተ​መላ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ይፈ​ር​ዳል፤ ስለ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ይራ​ራል፤ በያ​ሉ​በት መሳ​ለ​ቂያ ሆነው እንደ ኖሩ፥ ኀይ​ላ​ቸ​ውም እንደ ደከመ፥ በጠ​ላ​ትም እጅ እንደ ወደቁ አይ​ቶ​አ​ልና።


እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።


ጌዴ​ዎ​ንም በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ፤ ስሙ​ንም እስከ ዛሬ ድረስ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰላም” ብሎ ጠራው። እር​ሱም እስከ ዛሬ ድረስ ለኤ​ዝሪ አባት በሆ​ነ​ችው በኤ​ፍ​ራታ አለ።


አሁ​ንም አንተ ከአ​ን​ተም ጋር የመጡ የጌ​ታህ ብላ​ቴ​ኖች ማል​ዳ​ችሁ ተነሡ፤ ሲነ​ጋም ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ወደ መጣ​ች​ሁ​በት ሂዱ። ክፉ ነገ​ር​ንም በል​ብህ አታ​ኑር፤ በዐ​ይኔ ፊት ጻድቅ ነህና፥ በነ​ጋም ጊዜ ገሥ​ግ​ሣ​ችሁ መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ሂዱ” አለው። እነ​ር​ሱም ሄዱ።


ሳሙ​ኤ​ልም አንድ ድን​ጋይ ወስዶ በመ​ሴ​ፋና በአ​ሮ​ጌው ከተማ መካ​ከል አኖ​ረው፤ ስሙ​ንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረድ​ቶ​ናል” ሲል “አቤ​ን​ኤ​ዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድ​ኤት ማለት ነው።


跟着我们:

广告


广告