Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 2:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ያን ጊዜም አዳም አለ፥ “ይህች አጥ​ንት ከአ​ጥ​ንቴ ናት፤ ሥጋ​ዋም ከሥ​ጋዬ ናት፤ እር​ስዋ ከባ​ልዋ ተገ​ኝ​ታ​ለ​ችና ሚስት ትሁ​ነኝ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አዳምም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ይህች ዐጥንት ከዐጥንቴ፣ ሥጋም ከሥጋዬ ናት። ከወንድ ተገኝታለችና ‘ሴት’ ትባል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አዳምም አለ፥ “ይህች አጥንት ከአጥንቴ የተገኘች ናት፥ ከሥጋዬም የተገኘች ሥጋ ናት፤ ሴት ተብላ ትጠራ፥ ከወንድ የተገኘች ስለ ሆነች ‘ሴት’ ትባል” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አዳምም፥ “እነሆ በመጨረሻ እርስዋ ከአጥንቶቼ የተገኘች አጥንት ናት፤ ከሥጋዬም የተገኘች ሥጋ ናት፤ ከወንድ የተገኘች ስለ ሆነች ‘ሴት’ ትባል” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አዳምም አለ፤ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፤ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 2:23
6 交叉引用  

ላባም ያዕ​ቆ​ብን፥ “በእ​ው​ነት አንተ አጥ​ንቴ ሥጋ​ዬም ነህ፤ ከእኔ ጋር ተቀ​መጥ” አለው። አንድ ወር የሚ​ያ​ህ​ልም ከእ​ርሱ ጋር ተቀ​መጠ።


ለአ​ሚ​ሳ​ይም፦ አንተ የአ​ጥ​ንቴ ፍላ​ጭና የሥ​ጋዬ ቍራጭ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? በዘ​መ​ን​ህም ሁሉ በኢ​ዮ​አብ ፋንታ በፊቴ የሠ​ራ​ዊት አለቃ ሳት​ሆን ብት​ቀር ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ያድ​ር​ግ​ብኝ፤ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​ብኝ በሉት።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ ወደ ኬብ​ሮን ወደ ዳዊት መጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “እኛ የአ​ጥ​ን​ትህ ፍላጭ የሥ​ጋህ ቍራጭ ነን።


“ለሰ​ቂማ ሰዎች ሁሉ፦ ሰባ የሆ​ኑት የይ​ሩ​በ​ኣል ልጆች ሁሉ ቢገ​ዙ​አ​ችሁ ወይስ አንድ ሰው ቢገ​ዛ​ችሁ ምን ይሻ​ላ​ች​ኋል? ብላ​ችሁ ንገ​ሩ​አ​ቸው፤ ደግ​ሞም እኔ የአ​ጥ​ን​ታ​ችሁ ፍላጭ፥ የሥ​ጋ​ችሁ ቍራጭ እንደ ሆንሁ አስቡ።”


跟着我们:

广告


广告