Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 2:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም አለ፥ “ሰው ብቻ​ውን ይኖር ዘንድ መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ የሚ​ረ​ዳ​ውን ጓደኛ እን​ፍ​ጠ​ር​ለት እንጂ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ፣ “ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለምና የሚስማማውን ረዳት አበጅለታለሁ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ጌታ እግዚእብሔርም፦ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፥ የምትሆነውን ረዳት እፈጥርለታለሁ” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ቀጥሎም እግዚአብሔር አምላክ “ሰው ብቻውን መኖሩ መልካም አይደለም፤ ስለዚህ ረዳት ጓደኛ እፈጥርለታለሁ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እግዚእብሔር አምላክም አለ፤ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረት እንፍጠርለት።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 2:18
10 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ጠ​ረ​ውን ሁሉ እጅግ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ ስድ​ስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።


አዳ​ምም ለእ​ን​ስ​ሳት ሁሉ፥ ለሰ​ማይ ወፎ​ችም ሁሉ፥ ለም​ድር አራ​ዊ​ትም ሁሉ ስም አወ​ጣ​ላ​ቸው። ነገር ግን ለአ​ዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አል​ተ​ገ​ኘ​ለ​ትም ነበር።


አዳ​ምም አለ፥ “ከእኔ ጋር እን​ድ​ት​ሆን የሰ​ጠ​ኸኝ ሴት እር​ስዋ ከዛፉ ሰጠ​ች​ኝና በላሁ።”


ደግ ሚስትን ያገኘ ሞገስን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ደስታን ተቀበለ። ደግ ሴትን የፈታ ደስታን አጣ፥ አመንዝራዪቱንም የሚያኖር አላዋቂና ኀጢአተኛ ነው።


በሸ​መ​ገለ ጊዜ ስለ ድን​ግ​ል​ናው እን​ደ​ሚ​ያ​ፍር የሚ​ያ​ስብ ሰው ቢኖር እን​ዲህ ሊሆን ይገ​ባል፤ የወ​ደ​ደ​ውን ያድ​ርግ፤ ቢያ​ገ​ባም ኀጢ​አት የለ​በ​ትም።


እንዲሁም እናንተ ባሎች ሆይ! ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው።


አማትዋም ኑኃሚን አለቻት፦ ልጄ ሆይ፥ መልካም እንዲሆንልሽ ዕረፍት አልፈልግልሽምን?


跟着我们:

广告


广告