ዘፍጥረት 19:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 እነርሱም፥ “ወዲያ ሂድ፤ ከእኛ ጋር ልትኖር መጣህ እንጂ ልትገዛን አይደለም፤ አሁንም ከእነርሱ ይልቅ አንተን እናሠቃይሃለን” አሉት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 እነርሱም፣ “ዞር በል! ይህ ሰው ራሱ ትናንት ተሰድዶ የመጣ ነው፤ ዛሬ ደግሞ ዳኛ ልሁን ይላል። ዋ! በእነርሱ ካሰብነው የከፋ እንዳናደርስብህ!” አሉት፤ ከዚያም ሎጥን እየገፈታተሩ የበሩን መዝጊያ ለመስበር ተንደረደሩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 እነርሱም፦ “ወዲያ ሂድ” አሉት። ደግሞም እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው በእንግድነት ለመኖር መጣ፥ ፍርዱንም ይፈርድ ዘንድ ይፈልጋል፥ አሁን በአንተ ከእነርሱ ይልቅ ክፉ እናደርግብሃለን።” ሎጥንም እጅግ ተጋፉት፥ የደጁንም መዝጊያ ለመስበር ቀረቡ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ሰዎቹ ግን “አንተ ስደተኛ፥ ሂድ ወዲያ! ለመሆኑ ልናደርገው የሚገባንን ነገር የምትነግረን አንተ ማን ነህ? ሂድ ወዲያ፤ አለበለዚያ በእነርሱ ላይ ልናደርግ ካሰብነው የከፋ ነገር በአንተ ላይ እናደርጋለን” አሉት። በዚህ ዐይነት ሎጥን ወዲያ ገፍትረው በሩን ለመስበር ተነሣሡ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 እነርሱም፤ ወዲያ ሂድ አሉት። ደግሞም እንዲህ አሉ፤ ይህ ሰው በእንግድነት ለመኖር መጣ ፍርዱንም ይፈርድ ዘንድ ይፈልጋል አሁን በአንተ ከእነርሱ ይልቅ ክፉ እናደርግብሃለን። ሎጥንም እጅግ ተጋፉት የደጁንም መዝጊያ ለመስበር ቀረቡ። 参见章节 |