Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 19:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እነሆ፥ ባሪ​ያህ በፊ​ትህ ምሕ​ረ​ትን አግ​ኝቼ እን​ደ​ሆነ፥ ሰው​ነ​ቴ​ንም ታድ​ናት ዘንድ፥ ቸር​ነ​ት​ህን አብ​ዝ​ተ​ህ​ልኝ እንደ ሆነ፥ መከራ አግ​ኝ​ቶኝ እን​ዳ​ል​ጠፋ ወደ ተራራ ሸሽቼ ራሴን ማዳን አል​ች​ልም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እነሆ፤ እኔ ባሪያህ አንዴ በፊትህ ሞገስ አግኝቻለሁ፤ ሕይወቴን ለማዳን ታላቅ ርኅራኄ አድርገህልኛል፤ እኔ እንደ ሆንሁ ወደ ተራሮቹ ሸሽቼ ማምለጥ ስለማልችል የሚወርደው መዓት ደርሶ ያጠፋኛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እነሆ ባርያህ በፊትህ ሞገስን አግኝቶአል፥ ነፍሴን ለማዳን ያደረግህልኝን ምሕረትህንም አብዝተሃል፥ ክፉ እንዳያገኘኝና እንዳልሞት ወደ ተራራ ሸሽቼ አመልጥ ዘንድ አልችልም፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እኔ አገልጋያችሁ በፊታችሁ ሞገስ ስላገኘሁ ሕይወቴን ለማዳን ታላቅ ርዳታ አድርጋችሁልኛል፤ ነገር ግን ይህ ጥፋት ደርሶብኝ እሞታለሁ ብዬ ስለምሰጋ ወደዚያ ተራራ መሸሽ አልችልም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እነሆ ባሪያህ በፊትህ ሞገስን አግኝቶአል ነፍሴን ለማዳን ያደረግህልኝን ምሕረትህንም አብዝተሃል ክፋ እንዳያጋኘኝና እንዳልሞት ወደ ተራራ ሸሽቼ አመልጥ ዘንድ አልችልም

参见章节 复制




ዘፍጥረት 19:19
20 交叉引用  

እን​ግ​ዲህ በአ​ንቺ ምክ​ን​ያት መል​ካም ይሆ​ን​ልኝ ዘንድ፥ ስለ አን​ቺም ነፍሴ ትድን ዘንድ እኅቱ ነኝ በዪ።”


ሎጥም አላ​ቸው፥ “ጌቶች ሆይ፥ በጀ በሉኝ፤


እነሆ፥ ይህች ከተማ ወደ እር​ስዋ ሸሽቶ ለማ​ም​ለጥ ቅርብ ናት፤ እር​ስ​ዋም ትንሽ ናት፤ ነፍ​ሴን ለማ​ዳን ወደ እር​ስዋ ሸሽቼ ራሴን ላድን፤ ሰው​ነ​ቴም ከዳ​ነች ትንሽ አይ​ደ​ለ​ችም፤”


ሎጥም ከሴ​ጎር ወጣ፤ ከሁ​ለ​ቱም ሴቶች ልጆቹ ጋር በተ​ራራ ተቀ​መጠ፤ በሴ​ጎር መቀ​መ​ጥን ፈር​ቶ​አ​ልና እር​ሱና ሁለቱ ሴቶች ልጆቹ በዋሻ ተቀ​መጡ።


ዮሴ​ፍም በጌ​ታው ፊት ሞገ​ስን አገኘ፤ እር​ሱ​ንም ደስ ያሰ​ኘው ነበር፤ በቤ​ቱም ላይ ሾመው፤ ያለ​ው​ንም ሁሉ በእጁ ሰጠው።


ኖኅ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞገ​ስን አገኘ።


መል​ሰ​ውም፦ ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ያወ​ጣ​ውን አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተው ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ስለ ተከ​ተሉ፥ ስለ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥ ስለ አመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውም፥ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ባ​ቸው ይላሉ።” ያን​ጊ​ዜም ሰሎ​ሞን የፈ​ር​ዖ​ንን ልጅ ከዳ​ዊት ከተማ አው​ጥቶ በዚያ ወራት ለራሱ በሠ​ራው ቤት አስ​ገ​ባት።


እርሱም መልሶ “የማታምን ትውልድ ሆይ! እስከመቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደ እኔ አምጡት፤” አላቸው።


ዘመ​ዶ​ች​ዋና ጎረ​ቤ​ቶ​ች​ዋም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ቱን እን​ዳ​በ​ዛ​ላት በሰሙ ጊዜ ከእ​ር​ስዋ ጋር ደስ አላ​ቸው።


እን​ግ​ዲህ ስለ​ዚህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእና ጋር ከሆነ ማን ይች​ለ​ናል?


በዚ​ያም ቀን ቍጣዬ ይነ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ እተ​ዋ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ፊቴ​ንም ከእ​ነ​ርሱ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም መብል ይሆ​ናሉ፤ በዚ​ያም ቀን፦ በእ​ው​ነት አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቶ​ና​ልና፥ በእ​ኛም መካ​ከል የለ​ምና ይህ ክፉ ነገር ሁሉ አገ​ኘን እስ​ኪሉ ድረስ ብዙ ክፉ ነገ​ርና ጭን​ቀት ይደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ዋል።


ዳዊ​ትም በልቡ፥ “አንድ ቀን በሳ​ኦል እጅ እሞ​ታ​ለሁ፤ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ምድር ከመ​ሸሸ በቀር የሚ​ሻ​ለኝ የለም፤ ሳኦ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል አው​ራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተ​ዋል፤ እን​ዲ​ሁም ከእጁ እድ​ና​ለሁ” አለ።


跟着我们:

广告


广告