ዘፍጥረት 17:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ሕፃኑንም በስምንተኛው ቀን ትገርዙታላችሁ፤ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያይደለ፥ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም12 የሚመጣውም ትውልድ ሁሉ፣ ማንኛውም ወንድ ልጅ፣ ስምንት ቀን ሲሞላው ይገረዝ፤ እንደዚሁም በቤትህ የተወለደውና ከውጭ በገንዘብ የተገዛ ባዕድ ሁሉ ይገረዝ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 የስምንት ቀን ልጅ ይገረዝ፥ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያልሆነ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 በመጪው ዘመን የሚወለድ ወንድ ልጅ ሁሉ በተወለደ በስምንተኛው ቀን ይገረዝ፤ እንዲሁም በቤትህ የተወለዱና በቤትህ ሳይወለዱ ከውጪ በገንዘብ ተገዝተው የመጡ ባሪያዎች ሳይቀሩ በዚሁ ዐይነት ይገረዙ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 የስምንት ቀን ልጅ ይገረዝ፤ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያይደለ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገርዝ። 参见章节 |