Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 16:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሦራም አብ​ራ​ምን፥ “ከአ​ንተ የተ​ነሣ እገ​ፋ​ለሁ፤ እኔ አገ​ል​ጋ​ዬን በብ​ብ​ትህ ሰጠ​ሁህ፤ እንደ ፀነ​ሰ​ችም ባየች ጊዜ እኔን ማክ​በ​ርን ተወች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ይፍ​ረድ” አለ​ችው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ሦራም አብራምን፣ “ለደረሰብኝ በደል ተጠያቂው አንተ ነህ፤ አገልጋዬ ዕቅፍህ ውስጥ እንድትገባ እኔው ሰጠሁህ፤ አሁን ግን ይኸው ማርገዟን ስታውቅ ትንቀኝ ጀመር፤ እግዚአብሔር በአንተና በእኔ መካከል ይፍረድ” አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሦራም አብራምን፦ መገፋቴ በአንተ ላይ ይሁን፥ እኔ ባርያዬን በጉያህ ሰጠሁህ፥ እንዳረገዘችም ባየች ጊዜ እኔን በዓይንዋ አቃለለችኝ፥ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ አለችው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ሣራይም አብራምን “የደረሰብኝ በደል በአንተ ላይ ይሁን፤ እርስዋን ለአንተ የሰጠሁህ እኔ ራሴ ነኝ፤ እርስዋ ግን መፅነስዋን ካወቀችበት ጊዜ አንሥቶ እኔን መናቅ ጀምራለች፤ አሁንም ከእኔና ከአንተ ጥፋተኛው ማን እንደ ሆነ እግዚአብሔር ይፍረድ!” አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሦራም አብራምን፥ መገፋቴ በአንተ ላይ ይሁን፤ እኔ ባሪያዬን በብብትህ ሰጠሁህ፤ እንዳረገዘችም ባየች ጊዜ እኔን በዓይንዋ አቃለለችኝ፤ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ፥ መካከል ይፍረስ አለችው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 16:5
12 交叉引用  

አብ​ራ​ምም ወደ አጋር ገባ፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ እንደ ፀነ​ሰ​ችም ባየች ጊዜ እመ​ቤ​ቷን ማክ​በ​ር​ዋን ተወች።


አን​ተም ወደ እኔ ብታ​ልፍ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የና​ኮ​ርም አም​ላክ በእኛ መካ​ከል ይፍ​ረድ።” ያዕ​ቆ​ብም በአ​ባቱ በይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ ማለ።


እን​ዲ​ሁም ንጉሡ ኢዮ​አስ አባቱ ኢዮ​አዳ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ቸር​ነት አላ​ሰ​በም፤ ልጁ​ንም አዛ​ር​ያ​ስን አስ​ገ​ደ​ለው፤ እር​ሱም ሲሞት፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይየው፤ ይፍ​ረ​ደ​ውም” አለ።


አቤቱ፥ በጆ​ሮ​አ​ችን ሰማን፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም በዘ​መ​ና​ቸው በቀ​ድሞ ዘመን የሠ​ራ​ኸ​ውን ሥራ ነገ​ሩን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝብ ላይ ይፈ​ር​ዳል፤ አቤቱ አም​ላኬ፥ እንደ ጽድ​ቅህ ፍረ​ድ​ልኝ፤ እንደ የዋ​ህ​ነ​ቴም ይሁ​ን​ልኝ።


እነ​ር​ሱም፥ “በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ሽታ​ች​ንን አግ​ም​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና፥ ይገ​ድ​ለ​ንም ዘንድ ሰይ​ፍን በእጁ ሰጥ​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ል​ከ​ታ​ችሁ፤ ይፍ​ረ​ድ​ባ​ች​ሁም” አሉ​አ​ቸው።


በጽ​ዮን የም​ት​ኖር በእኔ ላይ የተ​ደ​ረገ ግፍና ሥቃይ በባ​ቢ​ሎን ላይ ይሁን ትላ​ለች፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ደሜ በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በሚ​ኖ​ሩት ላይ ይሁን ትላ​ለች።”


እኔ አል​በ​ደ​ል​ሁ​ህም፤ አንተ ግን ከእኔ ጋር ትዋጋ ዘንድ ክፉ አታ​ድ​ር​ግ​ብኝ፤ ፈራጁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና በአ​ሞን ልጆች መካ​ከል ዛሬ ይፍ​ረድ።”


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዳኛ ይሁን፤ በእ​ኔና በአ​ን​ተም መካ​ከል ይፍ​ረድ፤ አይ​ቶም ለእኔ ይፍ​ረድ፤ ከእ​ጅ​ህም ያድ​ነኝ።”


跟着我们:

广告


广告