Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 16:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሦራም አብ​ራ​ምን፥ “እነሆ፥ እን​ዳ​ል​ወ​ልድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘጋኝ፤ ከእ​ር​ስዋ ትወ​ልድ ዘንድ ወደ አገ​ል​ጋዬ ሂድ” አለ​ችው። አብ​ራ​ምም የሚ​ስ​ቱን የሦ​ራን ቃል ሰማ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አብራምንም፣ “እግዚአብሔር ልጅ እንዳልወልድ አድርጎኛል። ምናልባት በርሷ በኩል ልጆች አገኝ እንደሆን ሄደህ ከአገልጋዬ ጋራ ተኛ” አለችው። አብራምም ሦራ ባለችው ተስማማ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሦራም አብራምን፦ እነሆ፥ እንዳልወልድ እግዚአብሔር ዘጋኝ፥ ምናልባት ከእርሷ በልጅ እታነጽ እንደሆነ ወደ እርሷ ግባ አለችው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ስለዚህ ሣራይ አብራምን “እነሆ፥ እግዚአብሔር ልጅ እንዳልወልድ ከልክሎኛል፤ ወደዚህች ወደ አገልጋዬ ግባ፤ ምናልባት በእርስዋ በኩል ልጅ አገኝ ይሆናል” አለችው። አብራምም ሣራይ ባለችው ነገር ተስማማ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሦራም አብራምን፤ እነሆ እንዳልወልድ እግዚአብሔር ዘጋኝ ምናልባት ከእርስዋ በልጅ እታነጽ እንደ ሆነ ወደ እርስዋግባ አለችው፤

参见章节 复制




ዘፍጥረት 16:2
16 交叉引用  

ሦራም መካን ነበ​ረች፤ ልጆ​ችም አል​ነ​በ​ሩ​አ​ትም።


እባ​ር​ካ​ታ​ለ​ሁና፥ ከአ​ን​ተም ልጆ​ችን እሰ​ጣ​ታ​ለ​ሁና፤ አሕ​ዛ​ብና የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ከእ​ር​ስዋ ይወ​ጣሉ።”


እር​ሱም፥ “የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ወደ አንተ ተመ​ልሼ እመ​ጣ​ለሁ፤ ሚስ​ትህ ሣራም ልጅን ታገ​ኛ​ለች” አለ።


ታላ​ቂ​ቱም ታና​ሺ​ቱን አለ​ቻት፥ “አባ​ታ​ችን ሽማ​ግሌ ነው፤ በም​ድ​ርም ሁሉ እን​ዳ​ለው ልማድ ሊገ​ና​ኘን የሚ​ችል ሰው በም​ድር ላይ የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ብ​ር​ሃም ሚስት በሣራ ምክ​ን​ያት በአ​ቤ​ሜ​ሌክ ቤት ማኅ​ፀ​ኖ​ችን ሁሉ በፍ​ጹም ዘግቶ ነበ​ርና።


ይስ​ሐ​ቅም ስለ ሚስቱ ርብቃ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመነ፤ መካን ነበ​ረ​ችና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው፤ ሚስቱ ርብ​ቃም ፀነ​ሰች።


አዳ​ምም አለ፥ “ከእኔ ጋር እን​ድ​ት​ሆን የሰ​ጠ​ኸኝ ሴት እር​ስዋ ከዛፉ ሰጠ​ች​ኝና በላሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ምን አለው፥ “የሚ​ስ​ት​ህን ቃል ሰም​ተ​ሃ​ልና፥ ከእ​ርሱ እን​ዳ​ት​በላ ከአ​ዘ​ዝ​ሁህ ከዚያ ዛፍም በል​ተ​ሃ​ልና ምድር በሥ​ራህ የተ​ረ​ገ​መች ትሁን፤ በሕ​ይ​ወት ዘመ​ን​ህም ሁሉ በድ​ካም ከእ​ር​ስዋ ትበ​ላ​ለህ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ራሔ​ልን አሰ​ባት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተለ​መ​ናት፤ ማኅ​ፀ​ን​ዋ​ንም ከፈ​ተ​ላት፤ ፀነ​ሰ​ችም፤


ራሔ​ልም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈረ​ደ​ልኝ፤ ቃሌ​ንም ደግሞ ሰማ፤ ወንድ ልጅ​ንም ሰጠኝ” አለች፤ ስለ​ዚህ ስሙን ዳን ብላ ጠራ​ችው።


ሚስ​ትህ በቤ​ትህ እል​ፍኝ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ያ​ፈራ ወይን ትሆ​ና​ለች፤ ልጆ​ች​ህም በማ​ዕ​ድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወ​ይራ ተክል ይሆ​ናሉ።


ጌታው ሚስት አጋ​ብ​ቶት እንደ ሆነ ወን​ዶች ወይም ሴቶች ልጆች ብት​ወ​ል​ድ​ለት፥ ሚስ​ቱና ልጆቹ ለጌ​ታው ይገዙ፤ እር​ሱም ብቻ​ውን ነጻ ይውጣ።


በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ሽማግሌዎቹም፦ እኛ ምስክሮች ነን፣ እግዚአብሔር ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፣ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተ ልሔም ይጠራ።


跟着我们:

广告


广告