Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 16:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “ከብ​ዛቱ የተ​ነሣ እስ​ከ​ማ​ይ​ቈ​ጠር ድረስ ዘር​ሽን እጅግ አበ​ዛ​ለሁ፥” አላት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ደግሞም የእግዚአብሔርም መልአክ፣ “ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፤ ከብዛቱም የተነሣ ሊቈጠር አይችልም” አላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የእግዚአብሔር መልአክም፦ ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፥ ከብዛቱም የተነሣ አይቆጠርም አላት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ደግሞም እንዲህ አላት፤ “ማንም ሊቈጥረው እስከማይችል ድረስ ዘርሽን አበዛዋለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የእግዚአብሔር መልአክም፥ ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፥ ከብዛቱም የተነሣ አይቆጠርም አላት።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 16:10
25 交叉引用  

ዘር​ህ​ንም እንደ ባሕር አሸዋ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የባ​ሕር አሸ​ዋን ይቈ​ጥር ዘንድ የሚ​ችል ሰው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቈ​ጠ​ራል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም፥ “ወደ እመ​ቤ​ትሽ ተመ​ለሺ፤ ከእ​ጅ​ዋም በታች ራስ​ሽን ዝቅ አድ​ርጊ” አላት።


ስለ ይስ​ማ​ኤ​ልም እነሆ፥ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፤ እባ​ር​ከ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ እጅ​ግም አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዐሥራ ሁለት አለ​ቆ​ች​ንም ይወ​ል​ዳል፤ ታላቅ ሕዝ​ብም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


የባ​ሪ​ያ​ዪ​ቱን ልጅ ደግሞ ታላቅ ሕዝብ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ዘርህ ነውና።”


ልጄ ሲሞት አላ​የ​ውም ብላ ቀስት ተወ​ር​ውሮ የሚ​ደ​ር​ስ​በ​ትን ያህል ርቃ በአ​ን​ጻሩ እየ​ተ​መ​ለ​ከ​ተች፥ ፊት ለፊት ተቀ​መ​ጠች፤ ቃል​ዋ​ንም አሰ​ምታ አለ​ቀ​ሰች።


ተነሺ፤ ልጅ​ሽ​ንም አንሺ፤ በእ​ጅ​ሽም አጽ​ኚው፤ ትልቅ ሕዝብ አደ​ር​ገ​ዋ​ለ​ሁና።”


በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኛም አይ​ደ​ለም፤ በመ​ል​አ​ክም አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ራሱ ያድ​ና​ቸ​ዋል እንጂ። እርሱ ይወ​ዳ​ቸ​ዋ​ልና፥ ይራ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ል​ምና እርሱ ተቤ​ዣ​ቸው፤ ተቀ​በ​ላ​ቸ​ውም፤ በዘ​መ​ና​ቸ​ውም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አከ​በ​ራ​ቸው።


እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


በአ​ባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጅ እርሱ ገለ​ጠ​ልን እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ከቶ ያየው የለም።


እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም፤ ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኀይል ይሁን፤ አሜን።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ መጥቶ በኤ​ፍ​ራታ ባለ​ችው ለኤ​ዝሪ አባት ለኢ​ዮ​አስ በነ​በ​ረ​ችው ዛፍ በታች ተቀ​መጠ፤ ልጁም ጌዴ​ዎን ከም​ድ​ያ​ማ​ው​ያን ለማ​ሸሽ በወ​ይን መጭ​መ​ቂ​ያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤ ምድ​ያ​ም​ንም እንደ አንድ ሰው አድ​ር​ገህ ታጠ​ፋ​ለህ” አለው።


跟着我们:

广告


广告