Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ስለ ምር​ኮ​ኞ​ቹም መተ​ላ​ለፍ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ቃል የሚ​ፈሩ ሁሉ ወደ እኔ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እኔም እስከ ሠርክ መሥ​ዋ​ዕት ድረስ ዐዝኜ ተቀ​መ​ጥሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በደል ከፈጸሙት ምርኮኞች የተነሣም በእስራኤል አምላክ ቃል የተንቀጠቀጡት ሁሉ በዙሪያዬ ተሰበሰቡ፤ እኔም እስከ ሠርክ መሥዋዕት ድረስ እጅግ እንደ ደነገጥሁ በዚያው ተቀመጥሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በእስራኤል አምላክ ቃል የሚንቀጠቀጡ ሁሉ ስለ ምርኮኞቹ አለመታመን ወደ እኔ ተሰበሰቡ፥ እኔም እስከ ሠርክ መሥዋዕት ድረስ ደንግጬ ተቀመጥሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የሠርክ መሥዋዕት እስከሚቀርብበትም ጊዜ ድረስ በድንጋጤና በሐዘን ቈየሁ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ስለ ሠሩት ኃጢአት በተናገረው ቃል ከመፍራት የተነሣ ድንጋጤ አድሮባቸው የነበሩትም ሁሉ በዙሪያዬ ተሰበሰቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ስለ ምርኮኞቹም መተላለፍ የእስራኤልን አምላክ ቃል የሚፈሩ ሁሉ ወደ እኔ ተሰበሰቡ፤ እኔም እስከ ሠርክ መሥዋዕት ድረስ ደንግጬ ተቀመጥሁ።

参见章节 复制




ዕዝራ 9:4
13 交叉引用  

በፊ​ቴም ራስ​ህን አዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ በዚ​ህም ስፍራ በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ ቃሌን በሰ​ማህ ጊዜ ራስ​ህን አዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ ልብ​ስ​ህ​ንም ቀድ​ደህ በፊቴ አል​ቅ​ሰ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አሁ​ንም እንደ ጌታ​ዬና የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ትእ​ዛዝ እን​ደ​ሚ​ፈ​ሩት ምክር፥ ሴቶ​ችን ሁሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ወ​ለ​ዱ​ትን እን​ሰ​ድድ ዘንድ ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ጋር ቃል ኪዳን እና​ድ​ርግ። ተነሥ እንደ አም​ላ​ካ​ች​ንም ትእ​ዛዝ ገሥ​ፃ​ቸው፤ እንደ ሕጉም ያድ​ርጉ፤


ሦስት ቀንም ሳያ​ልፍ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃ​ያ​ኛው ቀን የይ​ሁ​ዳና የብ​ን​ያም ሰዎች ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተሰ​በ​ሰቡ። ሕዝ​ቡም ሁሉ ስለ​ዚህ ነገ​ርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት ባለው አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጡ።


አን​ዱን ጠቦት በነ​ግህ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ጠቦት በሠ​ርክ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገህ ታቀ​ር​በ​ዋ​ለህ።


ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ጠቦት በሠ​ርክ ታቀ​ር​በ​ዋ​ለህ፤ እንደ ነግ​ሁም የእ​ህ​ልና የመ​ጠጥ ቍር​ባን ታደ​ር​ግ​በ​ታ​ለህ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የእ​ሳት ቍር​ባን ይሆ​ናል።


ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ወደ የዋ​ሁና ወደ ጸጥ​ተ​ኛው፥ ከቃ​ሌም የተ​ነሣ ወደ​ሚ​ን​ቀ​ጠ​ቀጥ ሰው ከአ​ል​ሆነ በቀር ወደ ማን እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ?


በቃሉ የም​ት​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ይከ​ብር ዘንድ፦ ደስ​ታ​ች​ሁም ይገ​ለጥ ዘንድ፥ እነ​ር​ሱም ያፍሩ ዘንድ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁ​ንና የሚ​ጸ​የ​ፉ​አ​ች​ሁን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በሏ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በከ​ተ​ማ​ዪቱ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መካ​ከል እለፍ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ዋም ስለ ተሠ​ራው ኀጢ​አት ሁሉ በሚ​ያ​ለ​ቅ​ሱና በሚ​ተ​ክዙ ሰዎች ግን​ባር ላይ ምል​ክት ጻፍ አለው።


እነ​ሆም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አንዱ መጥቶ በሙ​ሴና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ፊት ወን​ድ​ሙን ወደ ምድ​ያ​ማ​ዊት ሴት ወሰ​ደው፤ እነ​ር​ሱም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዳጃፍ ያለ​ቅሱ ነበር።


ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም በዘ​ጠኝ ሰዓት ለጸ​ሎት በአ​ን​ድ​ነት ወደ ቤተ መቅ​ደስ ወጡ።


跟着我们:

广告


广告