Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 9:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አሁ​ንም ትበ​ረቱ ዘንድ፥ የም​ድ​ሩ​ንም ፍሬ ትበሉ ዘንድ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይወ​ር​ሱ​አት ዘንድ፥ ሴቶ​ችን ልጆ​ቻ​ች​ሁን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው አት​ስጡ፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ችሁ አት​ው​ሰዱ፤ ሰላ​ማ​ቸ​ው​ንና ደኅ​ን​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አትሹ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ። ብርቱዎች እንድትሆኑ፣ የምድሪቱን መልካም ነገር እንድትበሉና ለልጆቻችሁም የዘላለም ርስት እንድታወርሱ ከእነርሱ ጋራ ምንም ዐይነት ውል አታድርጉ’ ብለህ የሰጠኸውን ትእዛዝ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ፥ ሰላማቸውንና ደኅነንታቸውንም ለዘለዓለም አትሹ። ይህም እንድትበረቱ፥ የምድሩንም መልካም ነገር እንድትበሉ፥ ለልጆቻችሁ ለዘለዓለምም ውርስ እንድታወርሱ ነው።’”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁን በጋብቻ ለእነርሱ ወንዶች ልጆች አትስጡ፤ እናንተም ለወንዶች ልጆቻችሁ የእነርሱን ሴቶች ልጆች በጋብቻ አትውሰዱ፤ በማንኛውም ጊዜ ከምድሩ መልካም ነገር በልታችሁ ለልጆቻችሁ ዘላቂ ርስት አድርጋችሁ ለማስተላለፍ እንድትችሉ በማንኛውም ጊዜ ከእነርሱ ጋር የወዳጅነት ስምምነት አታድርጉ’ ሲሉ ነግረውን ነበር።

参见章节 复制




ዕዝራ 9:12
17 交叉引用  

አሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጉባኤ እስ​ራ​ኤል ሁሉ እያዩ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንም እየ​ሰማ፥ ይህ​ችን መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር ትወ​ርሱ ዘንድ፥ ለል​ጆ​ቻ​ች​ሁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታወ​ር​ሱ​አት ዘንድ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤ ፈል​ጉም።


ነቢዩ የአ​ናኒ ልጅ ኢዩ ሊገ​ና​ኘው ወጣ፤ ንጉ​ሡ​ንም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ታግ​ዛ​ለ​ህን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጠ​ላ​ውን ትወ​ድ​ዳ​ለ​ህን? ስለ​ዚ​ህም ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ቍጣ መጥ​ቶ​ብ​ሃል።


ለራ​ሳ​ቸ​ውና ለል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ወስ​ደ​ዋል፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ዘር ከም​ድር አሕ​ዛብ ጋር ደባ​ል​ቀ​ዋል፤ አስ​ቀ​ድ​ሞም አለ​ቆ​ቹና ሹሞቹ በዚህ መተ​ላ​ለፍ መጀ​መ​ሪያ ሆነ​ዋል” አሉኝ።


ከእ​ነ​ር​ሱና ከአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ቃል ኪዳን አታ​ድ​ርግ።


ደግ ሰው ለልጅ ልጅ ያወርሳል፥ የኀጢአተኞች ብልጽግና ግን ለጻድቃን ይደልባል።


ያለ ነውር ወደ እውነት በንጹሕ የሚሄድ፥ ልጆቹን ብፁዓን ያደርጋቸዋል።


እሽ ብት​ሉና ብት​ሰ​ሙኝ የም​ድ​ርን በረ​ከት ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤


በዘ​መ​ንህ ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሰላም እን​ደ​ሚ​ገ​ባ​ቸው አታ​ና​ግ​ራ​ቸው።


“ኤዶ​ማ​ዊዉ ወን​ድ​ምህ ነውና አት​ጸ​የ​ፈው፤ ግብ​ፃ​ዊ​ዉ​ንም በሀ​ገሩ ስደ​ተኛ ነበ​ር​ህና አት​ጸ​የ​ፈው።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር አት​ጋባ፤ ሴት ልጅ​ህን ለወ​ንድ ልጁ አት​ስጥ፥ ሴት ልጁ​ንም ለወ​ንድ ልጅህ አት​ው​ሰድ።


跟着我们:

广告


广告