ዕዝራ 9:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 በባሮችህ በነቢያት እጅ ያዘዝሃትን እንዲህ ስትል፦ ትወርሱአት ዘንድ የምትገቡባት ምድር በምድር አሕዛብ ርኵሰት የረከሰች ናት፤ በርኵሰታቸውም ከዳር እስከ ዳርቻዋ ድረስ መልተዋታል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ያቃለልነውም በባሮችህ በነቢያት አማካይነት፣ ‘ለመውረስ የምትገቡባት ምድር በሕዝቦቿ ርኩሰት ተበክላለች፤ ከዳር እስከ ዳርም በአስጸያፊ ድርጊታቸውና በርኩሰታቸው ተሞልታለች፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 በአገልጋዮችህ በነቢያት እንዲህ ስትል ያዘዝኸውን ‘ልትወርሱአት የምትገቡባት ምድር፥ በምድሩ ሕዝቦች ርኩሰት የረከሰች ምድር ናት፤ ከዳር እስከ ዳርም በርኩሰታቸውና በአጸያፊ ተግባራቸው ተሞልታለች። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 እነዚህም ትእዛዞች በአገልጋዮችህ በነቢያት አማካይነት የተሰጡ ነበሩ፤ ነቢያት አስቀድመው ‘የምትወርሱአት ምድር ከርኲሰት ሁሉ የነጻች አይደለችም፤ የሚኖሩባት ሕዝቦች ዳር እስከ ዳር በአጸያፊ ተግባር ሁሉ እንድትሞላ አድርገዋታል። 参见章节 |