Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 9:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አሁ​ንስ ከዚህ በኋላ ምን እን​ላ​ለን? አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ትተ​ና​ልና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “አሁን ግን አምላካችን ሆይ፤ ከዚህ በኋላ ምን እንላለን? ትእዛዞችህን አቃልለናልና፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ስለዚህ አምላካችን ሆይ ከዚህ በኋላ ምን እንላለን? ትእዛዛትህን ትተናልና፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “ነገር ግን አምላካችን ሆይ! እስከ አሁን ስለ ሆነው ነገር ሁሉ ምን ማለት እንችላለን? እነሆ፥ አሁንም እንደገና ትእዛዞችህ አላከበርንም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10-12 አሁንስ አምላካችን ሆይ፦ ‘ትወርሱአት ዘንድ የምትገቡባት ምድር በምድር አሕዛብ ርኵሰት ረክሳለች፤ ከዳር እስከ ዳርም ድረስ ከርኵሰታቸው፥ ከጸያፍ ሥራቸውም ተሞልታለች፤ አሁንም ትበረቱ ዘንድ፥ የምድሩንም ፍሬ ትበሉ ዘንድ፥ ለዘላለምም ለልጆቻችሁ ታወርሱአት ዘንድ ሴቶች ልጆቻችሁን ለልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለልጆቻችሁ አትውሰዱ፤ ሰላማቸውንና ደኅነንታቸውንም ለዘላለም አትሹ’ ብለህ በባሪያዎችህ በነቢያት ያዘዝኸውን ትእዛዝ ትተናልና ከዚህ በኋላ ምን እንላለን?

参见章节 复制




ዕዝራ 9:10
10 交叉引用  

ይሁ​ዳም አለ፦ “ለጌ​ታ​ችን ምን እን​መ​ል​ሳ​ለን? ምንስ እን​ና​ገ​ራ​ለን? ወይስ በምን እን​ነ​ጻ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን ኀጢ​አት ገለጠ። እነሆ፥ እኛም ጽዋው ከእ​ርሱ ዘንድ የተ​ገ​ኘ​በ​ትም ደግሞ ለጌ​ታ​ችን አገ​ል​ጋ​ዮቹ ነን።”


በባ​ሮ​ችህ በነ​ቢ​ያት እጅ ያዘ​ዝ​ሃ​ትን እን​ዲህ ስትል፦ ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ የም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር በም​ድር አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት የረ​ከ​ሰች ናት፤ በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውም ከዳር እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ መል​ተ​ዋ​ታል።


ባሪ​ያ​ዎቹ ነንና፥ አም​ላ​ካ​ችን ግን በባ​ር​ነ​ታ​ችን አል​ተ​ወ​ንም፤ ቀለ​ባ​ች​ንን ይሰ​ጡን ዘንድ፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ን​ንም ቤት ከፍ ከፍ ያደ​ርጉ ዘንድ፥ የተ​ፈ​ታ​ው​ንም ይጠ​ግኑ ዘንድ፥ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር ያደ​ር​ጉ​ልን ዘንድ በፋ​ርስ ነገ​ሥ​ታት ፊት ሞገ​ስን ሰጠን።


ነገር ግን ብዙ ዓመ​ታት ታገ​ሥ​ሃ​ቸው፤ በነ​ቢ​ያ​ት​ህም እጅ በመ​ን​ፈ​ስህ መሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸው፤ አላ​ደ​መ​ጡም፤ ስለ​ዚ​ህም በም​ድር አሕ​ዛብ እጅ አሳ​ል​ፈህ ሰጠ​ሃ​ቸው።


ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ችን፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሕግ​ህን አል​ጠ​በ​ቁም፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንና የመ​ሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸ​ውን ምስ​ክ​ር​ህ​ንም አል​ሰ​ሙም።


በተ​ጨ​ነቁ ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው፤


ሔት። ያል​ጠ​ፋ​ነው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረት የተ​ነሣ ነው፤ ርኅ​ራ​ኄው አያ​ል​ቅ​ምና።


አን​ደ​በት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለ​ምም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ በኦ​ሪት ላሉት እንደ ተነ​ገረ እና​ው​ቃ​ለን።


ጌታ ሆይ! እስ​ራ​ኤል ጀር​ባ​ውን ወደ ጠላ​ቶቹ ከመ​ለሰ እን​ግ​ዲህ ምን እላ​ለሁ?


跟着我们:

广告


广告