Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 8:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በላ​ያ​ች​ንም መል​ካም በሆ​ነው በአ​ም​ላ​ካ​ችን እጅ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጅ ከሌዊ ልጅ ከሞ​ሐሊ ልጆች ወገን የነ​በ​ረ​ውን አስ​ተ​ዋይ ሰው ሰራ​ብ​ያን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ዐሥራ ስም​ን​ቱን ልጆ​ቹ​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹን አመ​ጡ​ልን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 መልካሚቱ የአምላካችን እጅ በእኛ ላይ ስለ ነበረች፣ ከሞሖሊ ዘሮች የእስራኤል ልጅ የሌዊ ልጅ የሆነውን ሰራብያ ተብሎ የሚጠራውን አስተዋይ ሰው፣ ከርሱም ጋራ ዐሥራ ስምንት የሚሆኑ ወንዶች ልጆቹንና ወንድሞቹን አመጡልን፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የአምላካችን መልካም እጅ በላያችን ላይ ስለ ነበረች፥ የእስራኤል ልጅ የሌዊ ልጅ ከሆነው ከማሕሊ ልጆች ወገን የነበረውን አስተዋይ ሰው ሼሬብያን፥ ከእርሱም ጋር ዐሥራ ስምንት ልጆቹንና ወንድሞቹን አመጡልን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የእግዚአብሔር ታላቅ ኀይል ከእኛ ጋር ስለ ነበረ እነርሱ በቂ ችሎታ ያለውን፥ የማሕሊ ጐሣ የሆነውን ሼሬብያ ተብሎ የሚጠራውን ሌዋዊ ላኩልን፤ እርሱም ዐሥራ ስምንቱን ወንዶች ልጆቹንና ወንድሞቹን አስከትሎ ወደ እኛ መጣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በላያችንም መልካም በሆነው በአምላካችን እጅ ከእስራኤል ልጅ ከሌዊ ልጅ ከሞሖሊ ልጆች ወገን የነበረውን አስተዋይ ሰው ሰራብያን፥ ከእርሱም ጋር አሥራ ስምንቱን ልጆቹንና ወንድሞቹን አመጡልን።

参见章节 复制




ዕዝራ 8:18
22 交叉引用  

የሌዊ ልጆች፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት ሜራሪ።


የሜ​ራ​ሪም ልጆች፤ ሞሐሊ፥ ሙሲ፥ የሌ​ዋ​ው​ያን ወገ​ኖች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች እነ​ዚህ ናቸው።


አል​ዓ​ዛር ፊን​ሐ​ስን ወለደ፤ ፊን​ሐ​ስም አቢ​ሱን ወለደ፤


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት አስ​ተ​ዋ​ዮች የነ​በ​ሩ​ትን ሌዋ​ው​ያ​ንን ሁሉ ያጽ​ናና ነበር። የደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት እያ​ቀ​ረቡ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ እያ​መ​ሰ​ገኑ ሰባት ቀን በዓል አደ​ረጉ።


በን​ጉሡ ፊት በሚ​መ​ክ​ሩ​ትም፥ በኀ​ያ​ላ​ኑም፥ በን​ጉሡ አለ​ቆች ሁሉ ፊት በእኔ ላይ ምሕ​ረ​ቱን ላከ። እኔም በእኔ ላይ ባለ​ችው በአ​ም​ላኬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በረ​ታሁ፤ ከእ​ኔም ጋራ ይወጡ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆ​ቹን ሰበ​ሰ​ብሁ።


ይህም ዕዝራ ከባ​ቢ​ሎን ወጣ፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ የሰ​ጠ​ውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአ​ም​ላ​ኩም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና ንጉሡ ያሻ​ውን ሁሉ ሰጠው።


በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በአ​ን​ደ​ኛው ቀን ከባ​ቢ​ሎን ሊወጡ ጀመሩ፤ መል​ካ​ሚ​ቱም የአ​ም​ላኩ እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ።


ወደ አለ​ቆ​ቹም ወደ አል​ዓ​ዛር፥ ወደ አር​ኤል፥ ወደ ሰማ​አያ፥ ወደ ሀሎ​ናም፥ ወደ ያሪብ፥ ወደ ሄል​ና​ታን፥ ወደ ናታን፥ ወደ ዘካ​ር​ያስ፥ ወደ ሜሱ​ላም፥ ደግ​ሞም ወደ ዐዋ​ቂ​ዎቹ ወደ ዮያ​ሪ​ብና ወደ ሄል​ና​ታን ላክሁ።


ደግ​ሞም አሴ​ብ​ያ​ስን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ከሜ​ራሪ ልጆች ወገን የነ​በ​ረ​ውን ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ ሃያ​ውን ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ውን።


ንጉ​ሡ​ንም፥ “የአ​ም​ላ​ካ​ችን እጅ በሚ​ሹት ሁሉ ላይ ለመ​ል​ካም ነው፤ ኀይ​ሉና ቍጣው ግን እር​ሱን በሚ​ተዉ ሁሉ ላይ ነው” ብለን ተና​ግ​ረን ነበ​ርና፤ በመ​ን​ገድ ካለው ጠላት ያድ​ኑን ዘንድ ጭፍ​ራና ፈረ​ሰ​ኞች ከን​ጉሡ እለ​ምን ዘንድ አፍሬ ነበ​ርና።


ከካ​ህ​ና​ቱም አለ​ቆች ዐሥራ ሁለት ሰዎ​ችን፥ ሰራ​ብ​ያ​ንና ሐሳ​ብ​ያን፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ዐሥር ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ለየሁ፤


ዘኩር፥ ሰራ​ብያ፥ ሰባ​ንያ፤


የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም አለ​ቆች አሳ​ብያ፥ ሰር​ብያ፥ ኢያሱ፥ የቀ​ድ​ም​ኤ​ልም ልጆች፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእ​ዛዝ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው በእ​ነ​ርሱ ፊት ያከ​ብ​ሩና ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።


በቤ​ቱም አጠ​ገብ ላለው ለግ​ንብ በሮች፥ ለከ​ተ​ማ​ውም ቅጥር፥ ለም​ገ​ባ​በ​ትም ቤት እን​ጨት እን​ዲ​ሰ​ጠኝ ለን​ጉሡ ዱር ጠባቂ ለአ​ሳፍ ደብ​ዳቤ ይሰ​ጠኝ” አል​ሁት። ንጉ​ሡም ሁሉን ሰጠኝ። የከ​በ​ረች የአ​ም​ላኬ እጅ ከእኔ ጋር ነበ​ረ​ችና።


ደግሞ ኢያ​ሱና ባኒ፥ ሰራ​ብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሳባ​ታይ፥ ሆዲያ፥ መዕ​ሤያ፥ ቆሊጣ፥ ዓዛ​ርያ፥ ኢዮ​ዛ​ባድ፥ ሐናን፥ ፌል​ዕያ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ሕጉን ለሕ​ዝቡ ያስ​ተ​ምሩ ነበር፤ ሕዝ​ቡም በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው ቆመው ነበር።


ቤት በጥበብ ይሠራል፥ በዕውቀትም ይጸናል።


በመንገድህ ሁሉ ጥበብን ዕወቃት፥ እርስዋም መንገድህን ታቃናልሃለች።


እንደ ልቤም የሚ​ሆኑ ጠባ​ቂ​ዎ​ችን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዕ​ው​ቀ​ትና በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም ይጠ​ብ​ቁ​አ​ች​ኋል።


የሜ​ራ​ሪም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ሞሐሊ፥ ሙሲ። የሌ​ዋ​ው​ያን ወገ​ኖች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች እነ​ዚህ ናቸው።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በአ​እ​ምሮ እንደ ሕፃ​ናት አት​ሁኑ፤ ነገር ግን ለክፉ ነገር እንደ ሕፃ​ናት ሁኑ፤ በዕ​ው​ቀ​ትም ፍጹ​ማን ሁኑ።


跟着我们:

广告


广告