Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 6:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም አንድ ሆነው ነጽ​ተው ነበር፤ ሁሉም ንጹ​ሓን ነበሩ፤ ለም​ር​ኮ​ኞ​ቹም ልጆች ሁሉ፥ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ለካ​ህ​ናቱ፥ ለራ​ሳ​ቸ​ውም የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ዐረዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ካህናቱና ሌዋውያኑ ራሳቸውን አነጹ፤ ሁሉም በሥርዐቱ መሠረት ነጽተው ነበር። ሌዋውያኑም የፋሲካውን በግ ለምርኮኞቹ ሁሉ፣ ለካህናት ወንድሞቻቸውና ለራሳቸው ዐረዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ካህናቱና ሌዋውያኑ እንደ አንድ ሰው ሆነው እራሳቸውን አነጹ፥ ሁሉም ንጹሐን ነበሩ፥ ከምርኮ ለተመለሱ ሕዝቦች ሁሉ፥ ለወንድሞቻቸው ለካህናቱና ለራሳቸው ፋሲካውን አረዱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ካህናቱና ሌዋውያኑም ሁሉ በሥርዓቱ መሠረት ራሳቸውን አነጹ፤ ሌዋውያኑም በፋሲካው በዓል አከባበር ላይ ከምርኮ ለተመለሱት ሕዝብና ለካህናቱ፥ እንዲሁም ለራሳቸው የቀረቡትን እንስሶች ዐረዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ካህናቱና ሌዋውያኑም አንድ ሆነው ነጽተው ነበር፤ ሁሉም ንጹሐን ነበሩ፤ ለምርኮኞቹም ሁሉ፥ ለወንድሞቻቸውም ለካህናቱ፥ ለራሳቸውም የፋሲካውን በግ አረዱ።

参见章节 复制




ዕዝራ 6:20
7 交叉引用  

ነገር ግን ካህ​ናቱ ጥቂ​ቶች ነበ​ሩና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለመ​ግ​ፈፍ አይ​ች​ሉም ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ሌዋ​ው​ያን በቅን ልብ ከካ​ህ​ናት ይልቅ ይቀ​ደሱ ነበ​ርና ሥራው እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ፥ ካህ​ና​ቱም እስ​ኪ​ቀ​ደሱ ድረስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሌዋ​ው​ያን ያግ​ዙ​አ​ቸው ነበር።


የፋ​ሲ​ካ​ው​ንም በግ አረዱ፤ ካህ​ና​ቱም ከእ​ጃ​ቸው የተ​ቀ​በ​ሉ​ትን ደም ረጩ፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ቍር​በ​ቱን ገፈፉ።


ከዚ​ያም በኋላ ለራ​ሳ​ቸ​ውና ከእ​ነ​ርሱ ጋር ላሉ ለካ​ህ​ናቱ አዘ​ጋጁ፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ስቡን ለማ​ቅ​ረብ እስከ ሌሊት ድረስ ይሠሩ ነበ​ርና ስለ​ዚህ ሌዋ​ው​ያን ለራ​ሳ​ቸ​ውና ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ለአ​ሮን ልጆች ለካ​ህ​ናቱ አዘ​ጋጁ።


የአ​ሳ​ፍም ልጆች መዘ​ም​ራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሳ​ፍም፥ እንደ ኤማ​ንም የን​ጉ​ሡም ባለ ራእይ እንደ ነበ​ረው እንደ ኤዶ​ትም ትእ​ዛዝ በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው ነበሩ፤ በረ​ኞ​ቹም በሮ​ቹን ሁሉ ይጠ​ብቁ ነበር፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሌዋ​ው​ያን ያዘ​ጋ​ጁ​ላ​ቸው ነበ​ርና ከአ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ይርቁ ዘንድ አያ​ስ​ፈ​ል​ጋ​ቸ​ውም ነበር።


ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጠርቶ አላ​ቸው፥ “ሂዱና በየ​ወ​ገ​ና​ችሁ ጠቦት ውሰዱ፤ ለፋ​ሲ​ካም እረ​ዱት።


እር​ሱም እንደ እነ​ዚያ ሊቃነ ካህ​ናት አስ​ቀ​ድሞ ስለ ራሱ ኀጢ​አት በኋ​ላም ስለ ሕዝቡ ኀጢ​አት ዕለት ዕለት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሊያ​ቀ​ርብ አያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውም፤ ራሱን ባቀ​ረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድ​ር​ጎ​አ​ልና።


跟着我们:

广告


广告