Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 6:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ንጉ​ሡም ዳር​ዮስ እንደ ላከው ቃል፥ በዚ​ያን ጊዜ በወ​ንዝ ማዶ ያለ ገዥ ተን​ት​ናይ ደግሞ አስ​ተ​ር​ቡ​ዝ​ናይ ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም እን​ዲሁ ተግ​ተው አደ​ረጉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚያም ንጉሡ ዳርዮስ ባዘዘው መሠረት በኤፍራጥስ ማዶ አገረ ገዥ የነበረው ተንትናይ፣ ሰተርቡዝናይና ተባባሪዎቻቸው ሥራው በትጋት እንዲፈጸም አደረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ከዚያ በኋላ በወንዝ ማዶ ያለ አካባቢ ገዢ ታትናይ፥ ሽታርቦዝናይና ተባባሪዎቻቸው ንጉሡ ዳርዮስ እንደ ላከው ቃል፥ እንዲሁ ተግተው አደረጉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከዚህ በኋላ አገረ ገዢው ታተናይ፥ ሸታርቦዝናይና የእነርሱም ተባባሪዎች የሆኑ ባለሥልጣኖች ንጉሠ ነገሥቱ እንዳዘዛቸው ሁሉንም ነገር ፈጸሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ንጉሡም ዳርዮስ እንደ ላከው ቃል፥ በዚያን ጊዜ በወንዝ ማዶ ያለ ገዥ ተንትናይ፥ ደግሞ ሰተርቡዝናይ እና ተባባሪዎቻቸው እንዲሁ ተግተው አደረጉ።

参见章节 复制




ዕዝራ 6:13
9 交叉引用  

የን​ጉ​ሡም የአ​ር​ተ​ሰ​ስታ መል​እ​ክ​ተኛ በደ​ረሰ ጊዜ በአ​ዛዡ በሬ​ሁ​ምና በጸ​ሓ​ፊው በሲ​ም​ሳይ፥ በተ​ባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ፊት መል​እ​ክ​ቱን ባነ​በበ ጊዜ ፈጥ​ነው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አይ​ሁድ በፈ​ረስ ሄዱ፤ በኀ​ይ​ልም አስ​ተ​ዉ​አ​ቸው።


አዛዡ ሬሁም፥ ጸሓ​ፊ​ውም ሲም​ሳይ፥ የቀ​ሩ​ትም ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸው፥ ዲና​ው​ያን፥ አፈ​ር​ሳ​ት​ካ​ዋ​ያን፥ ጠር​ፈ​ላ​ው​ያን፥ አፈ​ር​ሳ​ው​ያን፥ አር​ካ​ው​ያን፥ ባቢ​ሎ​ና​ው​ያን፥ ሱስ​ና​ካ​ው​ያን፥ ዴሐ​ው​ያን፥ ኤላ​ማ​ው​ያን፥


በዚ​ያም ጊዜ በወ​ንዝ ማዶ የነ​በ​ረው ገዥ ተን​ት​ናይ፥ ደግሞ አስ​ተ​ር​ቡ​ዝ​ናይ ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ወደ እነ​ርሱ መጥ​ተው፥ “ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ ማን አዘ​ዛ​ችሁ? የም​ት​ሠ​ሩ​በ​ት​ንስ ሥል​ጣን ማን ሰጣ​ችሁ?” አሉ​አ​ቸው።


በወ​ንዙ ማዶ የነ​በ​ረው ገዥ ተን​ት​ናይ፥ ደግሞ አስ​ተ​ር​ቡ​ዝ​ናይ፥ ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በወ​ንዙ ማዶ የነ​በ​ሩት አፈ​ር​ስ​ካ​ው​ያ​ንም ወደ ንጉሡ ወደ ዳር​ዮስ የላ​ኩት የደ​ብ​ዳ​ቤው ቃል ይህ ነበረ።


“አሁ​ንም አንተ በወ​ንዝ ማዶ ያለ​ኸው የሀ​ገሩ ገዥ ተን​ት​ናይ ደግሞ አሰ​ተ​ር​ቡ​ዝ​ናይ በወ​ንዝ ማዶም ያሉ ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ችሁ አፈ​ር​ስ​ካ​ው​ያን ከዚያ ራቁ፤


ንጉሥ እንደ መሆኑ ኀይል አለ​ውና፤ ይህ​ንስ ለምን ታደ​ር​ጋ​ለህ? ማን ይለ​ዋል?


跟着我们:

广告


广告