Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 5:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 አሁ​ንም ይህ ነገር በን​ጉሡ ዐይን መል​ካም ቢሆን ይህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይሠራ ዘንድ ከን​ጉሡ ከቂ​ሮስ ታዝዞ እንደ ሆነ በባ​ቢ​ሎን ባለው በን​ጉሡ ቤተ መዛ​ግ​ብት ይመ​ር​መር፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር ንጉሡ ፈቃ​ዱን ይላ​ክ​ልን።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 አሁንም ንጉሡን ደስ የሚያሠኘው ቢሆን፣ ይህ የእግዚአብሔር ቤት በኢየሩሳሌም እንዲሠራ ንጉሥ ቂሮስ በርግጥ ትእዛዝ ሰጥቶ እንደ ሆነ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ግምጃ ቤት የተቀመጡት መዛግብት እንዲመረመሩ ያድርግ፤ ከዚያም ንጉሡ ስለዚህ ጕዳይ የወሰነውን ይላክልን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 “አሁንም ይህ ነገር በንጉሡ ዐይን መልካም ቢሆን ይህ የእግዚአብሔር ቤት በኢየሩሳሌም እንዲሠራ ከንጉሡ ከቂሮስ ታዝዞ እንደሆነ በባቢሎን ባለው በንጉሡ ቤተ መዛግብት ይመርመር፥ ስለዚህም ነገር ንጉሡ ፈቃዱን ይላክልን።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 “ንጉሥ ሆይ! እንግዲህ በእርግጥ ይህ ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ይሠራ ዘንድ ንጉሥ ቂሮስ የሰጠው ትእዛዝ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ በባቢሎን ቤተ መንግሥት የጽሑፍ ማስረጃዎችን አስመርምረህ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ዐይነት ውሳኔ ቢሰጥ እንደምትፈቅድ ታስታውቀን ዘንድ እንለምናለን።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 አሁንም ይህ ነገር በንጉሡ ዓይን መልካም ቢሆን ይህ የእግዚአብሔር ቤት በኢየሩሳሌም ይሠራ ዘንድ ከንጉሡ ከቂሮስ ታዝዞ እንደ ሆነ በባቢሎን ባለው በንጉሡ ቤተ መዛግብት ይመርመር፤ ስለዚህም ነገር ንጉሡ ፈቃዱን ይላክልን።”

参见章节 复制




ዕዝራ 5:17
4 交叉引用  

በአ​ባ​ቶ​ችህ ታሪክ መጽ​ሐፍ ምር​መራ ይደ​ረግ፤ በዚ​ያም በታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ይህች ከተማ ዐመ​ፀኛ እንደ ሆነች፥ ነገ​ሥ​ታ​ት​ንና አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ንም እንደ ጎዳች፥ ከጥ​ን​ቱም የገ​ባ​ሮች ሽፍ​ት​ነት በእ​ር​ስዋ እንደ ተጀ​መረ ታገ​ኛ​ለህ፤ ታው​ቃ​ለ​ህም፤ ስለ​ዚ​ህም ይህች ከተማ ፈርሳ ነበር።


እኔም አዝ​ዣ​ለሁ፤ ተመ​ረ​መ​ረም፤ ይህ​ችም ከተማ ከጥ​ንት ጀምራ በነ​ገ​ሥ​ታት ላይ ዐመ​ፀኛ እንደ ነበ​ረች፥ በእ​ር​ስ​ዋም ዐመ​ፅና ሽፍ​ት​ነት እንደ ተደ​ረገ ተገኘ።


跟着我们:

广告


广告