Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አሁ​ንም ከአ​ንተ ዘንድ የወጡ አይ​ሁድ ወደ እኛ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ መጡ ጌታ​ቸው ንጉሡ ይወቅ፤ ዐመ​ፀ​ኛ​ዪ​ቱ​ንና እጅ​ግም የከ​ፋ​ች​ቱን ከተማ ይሠ​ራሉ፤ ቅጥ​ር​ዋ​ንም ያድ​ሳሉ፤ መሠ​ረ​ቷ​ንም ጠገኑ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከአንተ ዘንድ ወደ እኛ የመጡት አይሁዳውያን ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ ዐመፀኛና ርኩስ ከተማ እንደ ገና በመሥራት ላይ ናቸው፤ ቅጥሮቿንም እንደ ገና በመሥራትና መሠረቶቿንም በመጠገን ላይ መሆናቸው በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከአንተ ዘንድ የመጡ አይሁድ ወደ እኛ ወደ ኢየሩሳሌም እንደመጡ በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ዓመፀኛይቱንና ክፉይቱን ከተማ በመስራት፥ ቅጥሮቿንም በማደስ፥ መሠረትዋንም በመጠገን ላይ ናቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 “ከግርማዊነትዎ ዘንድ የመጡት አይሁድ እዚህ ኢየሩሳሌም የደረሱ መሆናቸው በግርማዊነትዎ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ያቺን ዐመፀኛና ክፉ ከተማ እንደገና በመሥራት ላይ ናቸው፤ ቅጽሮቹን በመጠገንና የቤተ መቅደስዋንም መሠረት በመጣል ላይ ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አሁንም ከአንተ ዘንድ የወጡ አይሁድ ወደ እኛ ወደ ኢየሩሳሌም እንደ መጡ ንጉሡ ይወቅ፤ ዓመፀኛይቱንና እጅግም የከፋችቱን ከተማ ይሠራሉ፤ ቅጥርዋንም ያድሳሉ፤ መሠረትዋንም ይጠግናሉ።

参见章节 复制




ዕዝራ 4:12
22 交叉引用  

የከ​ን​ፈር ቃል ለሰ​ልፍ ምክ​ርና ኀይል እን​ደ​ሚ​ሆን ትና​ገ​ራ​ለህ፤ አሁ​ንም በእኔ ላይ ያመ​ፅ​ኸው በማን ተማ​ም​ነህ ነው?


በእ​ር​ሱም ዘመን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወጣ፤ ኢዮ​አ​ቄ​ምም ሦስት ዓመት ተገ​ዛ​ለት፤ ከዚ​ያም በኋላ ዘወር አለና ዐመ​ፀ​በት።


ደግ​ሞም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም አም​ሎት በነ​በ​ረው በን​ጉሡ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ላይ ዐመፀ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​መ​ለስ አን​ገ​ቱን አደ​ነ​ደነ፤ ልቡ​ንም አጠ​ነ​ከረ።


ለን​ጉሡ ለአ​ር​ተ​ሰ​ስታ የላ​ኩት የደ​ብ​ዳቤ ቃልም ይህ ነው፥ “በወ​ንዝ ማዶ ያሉት ሰዎች ባሪ​ያ​ዎ​ችህ፤


በአ​ባ​ቶ​ችህ ታሪክ መጽ​ሐፍ ምር​መራ ይደ​ረግ፤ በዚ​ያም በታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ይህች ከተማ ዐመ​ፀኛ እንደ ሆነች፥ ነገ​ሥ​ታ​ት​ንና አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ንም እንደ ጎዳች፥ ከጥ​ን​ቱም የገ​ባ​ሮች ሽፍ​ት​ነት በእ​ር​ስዋ እንደ ተጀ​መረ ታገ​ኛ​ለህ፤ ታው​ቃ​ለ​ህም፤ ስለ​ዚ​ህም ይህች ከተማ ፈርሳ ነበር።


እኔም አዝ​ዣ​ለሁ፤ ተመ​ረ​መ​ረም፤ ይህ​ችም ከተማ ከጥ​ንት ጀምራ በነ​ገ​ሥ​ታት ላይ ዐመ​ፀኛ እንደ ነበ​ረች፥ በእ​ር​ስ​ዋም ዐመ​ፅና ሽፍ​ት​ነት እንደ ተደ​ረገ ተገኘ።


በዚ​ያም ጊዜ በወ​ንዝ ማዶ የነ​በ​ረው ገዥ ተን​ት​ናይ፥ ደግሞ አስ​ተ​ር​ቡ​ዝ​ናይ ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ወደ እነ​ርሱ መጥ​ተው፥ “ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ ማን አዘ​ዛ​ችሁ? የም​ት​ሠ​ሩ​በ​ት​ንስ ሥል​ጣን ማን ሰጣ​ችሁ?” አሉ​አ​ቸው።


እነ​ዚ​ያ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፦ ‘ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ ማን አዘ​ዛ​ችሁ? የም​ት​ሠ​ሩ​በ​ት​ንስ ሥል​ጣን ማን ሰጣ​ችሁ?’ ብለን ጠየ​ቅ​ና​ቸው።


እነ​ር​ሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከም​ርኮ የተ​ረ​ፉት ቅሬ​ታ​ዎች በታ​ላቅ መከ​ራና ስድብ አሉ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር ፈር​ሶ​አል፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ለ​ዋል” አሉኝ።


“አን​ተና አይ​ሁድ ዓመፃ እን​ድ​ታ​ስቡ፥ ስለ​ዚ​ህም ቅጥ​ሩን እን​ድ​ት​ሠራ፥ ንጉ​ሣ​ቸ​ውም ትሆን ዘንድ እን​ድ​ት​ወ​ድድ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ተሰ​ም​ቶ​አል።


ከፊ​ቱም አው​ጥቶ እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ላይ ሆኖ​አ​ልና፤ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።


“ነቢ​ያ​ትን የም​ት​ገ​ድ​ሊ​ያ​ቸው፥ ወደ አንቺ የተ​ላ​ኩ​ትን ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም የም​ት​ደ​በ​ድ​ቢ​ያ​ቸው ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ዶሮ ጫጩ​ቶ​ች​ዋን ከክ​ን​ፍዋ በታች እን​ደ​ም​ት​ሰ​በ​ስብ ልጆ​ች​ሽን ልሰ​በ​ስ​ባ​ቸው ምን ያህል ወደ​ድሁ? ነገር ግን እንቢ አላ​ችሁ።


ይህን ሰው ሲሳ​ደ​ብና ወን​ጀል ሲሠራ፥ አይ​ሁ​ድ​ንም ሁሉ በየ​ሀ​ገሩ ሲያ​ውክ፥ ናዝ​ራ​ው​ያን የተ​ባ​ሉት ወገ​ኖች የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩ​ት​ንም ክህ​ደት ሲያ​ስ​ተ​ምር አግ​ኝ​ተ​ነ​ዋል።


ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ።


跟着我们:

广告


广告