Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 10:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የስ​ደ​ተ​ኞ​ቹም ልጆች እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ ካህኑ ዕዝራ፥ የአ​ባ​ቶ​ችም ቤቶች አለ​ቆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ሁሉም በየ​ስ​ማ​ቸው ተለዩ፤ በዐ​ሥ​ረ​ኛ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ነገ​ሩን ይመ​ረ​ምሩ ዘንድ ተቀ​መጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ስለዚህ ምርኮኞቹ እንደ ተባለው አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራም ከእያንዳንዱ የቤተ ሰብ ምድብ አንዳንድ የቤተ ሰብ ኀላፊ የሆነ ሰው መረጠ፤ ሁሉም በየስማቸው ተመዘገቡ። ከዚያም በዐሥረኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ጕዳዩን ለመመርመር ተቀመጡ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ምርኮኞቹም እንዲህ አደረጉ፥ ካህኑ ዕዝራ፥ የአባቶችን መሪዎች መረጠ፤ በየአባቶቻቸው ቤቶች ተለዩ፥ ሁሉም በየስማቸው ተጻፉ፥ በአሥረኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ነገሩን ሊመረምሩ ተቀመጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከምርኮ የተመለሱት ሁሉ ይህንኑ ዕቅድ ለመቀበል ተስማሙ፤ ስለዚህም ካህኑ ዕዝራ ከጐሣ መሪዎች መካከል መርጦ አስፈጻሚዎችን በመሾም ስም ዝርዝራቸውን መዝግቦ አኖረ፤ እነርሱም ዐሥረኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን ጉዳዩን መመርመር ጀመሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ምርኮኞቹም እንዲህ አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራም የአባቶችም ቤቶች አለቆች በየአባቶቻቸው ቤቶች ተለዩ፤ ሁሉም በየስማቸው ተጻፉ፤ በአሥረኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ነገሩን ይመረምሩ ዘንድ ተቀመጡ።

参见章节 复制




ዕዝራ 10:16
6 交叉引用  

ነገር ግን የአ​ሣ​ሄል ልጅ ዮና​ታ​ንና የቴ​ቁዋ ልጅ የሐ​ዝያ ስለ​ዚህ ነገር ከእኔ ጋር ናቸው፤ ሜሱ​ላ​ምና ሌዋ​ዊው ሰባ​ታ​ይም ይረ​ዱ​አ​ቸው ነበር።


እስከ መጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር እስከ መጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ድረስ ሠር​ተው እን​ግ​ዶ​ቹን ሴቶች ያገ​ቡ​ትን ሰዎች ሁሉ መር​ም​ረው ጨረሱ።


ለድ​ሃ​ዎች አባት ነበ​ርሁ፥ የማ​ላ​ው​ቀ​ው​ንም ሰው ክር​ክር መረ​መ​ርሁ።


“ሕጋ​ችን አስ​ቀ​ድሞ ሳይ​ሰማ፤ የሠ​ራ​ው​ንም ሳያ​ውቅ በሰው ይፈ​ር​ዳ​ልን?”


ትፈ​ል​ጋ​ለህ ትመ​ረ​ም​ራ​ለ​ህም፤ ትጠ​ይ​ቃ​ለ​ህም፤ እነ​ሆም፥ እው​ነት ቢሆን፥ ይህም ክፉ ነገር በመ​ካ​ከ​ልህ እንደ ተደ​ረገ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥


የዚ​ያ​ችን ሀገር ሰዎች በሰ​ይፍ ስለት ፈጽሞ ትመ​ታ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ሀገ​ሪ​ቱን፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ ትረ​ግ​ማ​ለህ።


跟着我们:

广告


广告