Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 10:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም በጉ​ባ​ኤው ፋንታ ሁሉ ይቁሙ፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር የአ​ም​ላ​ካ​ችን ጽኑ ቍጣ ከእኛ ይመ​ለስ ዘንድ እን​ግ​ዶ​ቹን ሴቶች ያገ​ቡት በከ​ተ​ሞ​ቻ​ችን ያሉት ሁሉ በተ​ቀ​ጠ​ረው ጊዜ ይምጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የከ​ተ​ማው ሁሉ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ፈራ​ጆች ይምጡ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስለዚህ ሹሞቻችን በማኅበሩ ሁሉ ምትክ መደረግ ያለበትን ያድርጉ። ከዚያም፣ በዚህ የተነሣ የመጣው የአምላካችን ብርቱ ቍጣ ከእኛ እስኪመለስ ድረስ፣ በየከተሞቻችን ያሉ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ ሁሉ በየከተማው ካሉት ሽማግሌዎችና ዳኞች ጋራ በተወሰነው ቀን ይምጡ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አለቆቻችንም ለጉባኤው ሁሉ ይቁሙ፥ ስለዚህም ነገር የአምላካችን የነደደው ቁጣ ከእኛ እንዲመለስ፥ እያንዳንዳቸው በከተሞቻችን ያሉ እንግዶቹን ሴቶች ያገቡት ሁሉ በተቀጠረው ጊዜ ይምጡ፥ ከእነርሱም ጋር የከተማ ሽማግሌዎችና ፈራጆች ይምጡ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለዚህ አለቆቻችን በዚሁ በኢየሩሳሌም ጉዳዩን ያጥኑት፤ ከዚህም በኋላ ባዕድ ሴት ያገባ ሁሉ እያንዳንዱ በሚሰጠው የቀጠሮ ቀን ከሚኖርባት ከተማ መሪዎችና ዳኞች ጋር እየመጣ ውሳኔውን ይቀበል፤ እግዚአብሔር የተቈጣበትም ሁኔታ ሁሉ በዚሁ ዐይነት ይበርዳል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አለቆቻችንም በጉባኤው ሁሉ ፋንታ ይቁሙ፤ ስለዚህም ነገር የአምላካችን ጽኑ ቍጣ ከእኛ ይመለስ ዘንድ እንግዶቹን ሴቶች ያገቡት በከተሞቻችን ያሉት ሁሉ በተቀጠረው ጊዜ ይምጡ፤ ከእነርሱም ጋር የከተማ ሁሉ ሽማግሌዎችና ፈራጆች ይምጡ።”

参见章节 复制




ዕዝራ 10:14
14 交叉引用  

ነገር ግን ምናሴ ስላ​ስ​ቈ​ጣው ነገር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በይ​ሁዳ ላይ ከነ​ደ​ደው ከታ​ላቁ ቍጣው ትኵ​ሳት አል​ተ​መ​ለ​ሰም።


አሁ​ንም ስሙ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በላ​ያ​ችሁ ነድ​ዶ​አ​ልና ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ የወ​ሰ​ዳ​ች​ኋ​ቸ​ውን ምር​ኮ​ኞች መልሱ።”


አሁ​ንም የቍ​ጣ​ውን መቅ​ሠ​ፍት ከእኛ እን​ዲ​መ​ልስ ከእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ቃል ኪዳን አደ​ርግ ዘንድ በልቤ አስ​ቤ​አ​ለሁ።


አሁ​ንም እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ አን​ገ​ታ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ስጡ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ወደ ተቀ​ደ​ሰው ወደ መቅ​ደሱ ግቡ፤ ጽኑ ቍጣ​ው​ንም ከእ​ና​ንተ እን​ዲ​መ​ልስ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ።


ነገር ግን የሕ​ዝቡ ቍጥር ብዙ ነው፤ ጊዜ​ውም የት​ልቅ ዝናብ ጊዜ ነው፤ በሜ​ዳም ልን​ቆም አን​ች​ልም፤ በዚ​ህም ነገር እጅግ በድ​ለ​ና​ልና ይህ ሥራ የአ​ንድ ወይም የሁ​ለት ቀን ሥራ አይ​ደ​ለም።


ነገር ግን የአ​ሣ​ሄል ልጅ ዮና​ታ​ንና የቴ​ቁዋ ልጅ የሐ​ዝያ ስለ​ዚህ ነገር ከእኔ ጋር ናቸው፤ ሜሱ​ላ​ምና ሌዋ​ዊው ሰባ​ታ​ይም ይረ​ዱ​አ​ቸው ነበር።


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ትላ​ለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈ​ጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ ቍጣ​ህ​ንም ከእኔ መል​ሰ​ሃ​ልና፥ ዳግ​መ​ኛም ይቅር ብለ​ኸ​ኛ​ልና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ስላ​ፈ​ረሱ የሕ​ዝ​ቡን አለ​ቆች ሁሉ ወስ​ደህ በፀ​ሐይ ፊት ቅጣ​ቸው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ ከእ​ስ​ራ​ኤል ይር​ቃል።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ቅ​ሠ​ፍቱ ቍጣ ይመ​ለስ ዘንድ፥ ለአ​ባ​ቶ​ች​ህም እንደ ማለ​ላ​ቸው ይም​ርህ ዘንድ፥ ይራ​ራ​ል​ህም ዘንድ፥ ያበ​ዛ​ህም ዘንድ፥ ርጉም ከሆ​ነው አን​ዳች ነገር በእ​ጅህ አት​ንካ።


ወደ ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት በዚ​ያም ዘመን ወደ አሉ ፈራ​ጆች መጥ​ተህ ትጠ​ይ​ቃ​ለህ፤ እነ​ር​ሱም የፍ​ር​ዱን ነገር ይነ​ግ​ሩ​ሃል።


በላ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ተመ​ለሰ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ዔሜ​ቃ​ኮር ተብሎ ተጠራ።


跟着我们:

广告


广告