ሕዝቅኤል 9:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ሲገድሉም እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግንባሬ ተደፍቼ፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ቅሬታ ሁሉ ታጠፋለህን?” ብዬ ጮኽሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 እነርሱ እየገደሉ እኔም ብቻዬን ሳለሁ፣ በግንባሬ ተደፍቼ፣ “ወዮ! ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ በኢየሩሳሌም ላይ መዓትህን አውርደህ የእስራኤልን ቅሬታዎች ሁሉ ልታጠፋ ነውን?” በማለት ጮኽሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 እነርሱ ሲገድሉ እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግምባሬ ተደፍቼ ጮኽሁ፥ እንዲህም አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ትሩፍ ሁሉ ታጠፋለህን? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ግድያውም በሚፈጸምበት ጊዜ እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግንባሬም ወደ መሬት ተደፍቼ በመጮኽ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ! በእስራኤል የተረፉትን ሁሉ እስክትፈጅ ድረስ በኢየሩሳሌም ላይ ይህን ያህል ትቈጣለህን?” አልኩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ሲገድሉም እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግምባሬ ተደፍቼ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ቅሬታ ሁሉ ታጠፋለህን? ብዬ ጮኽሁ። 参见章节 |