ሕዝቅኤል 9:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 እርሱም፥ “እያንዳንዳቸው የሚያጠፉባት መሣሪያን በእጃቸው ይዘው ከተማዪቱን የሚቀሥፉ ይቅረቡ” ብሎ በታላቅ ድምፅ በጆሮዬ ጮኸ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ከዚያም እኔ እየሰማሁ ከፍ ባለ ድምፅ፣ “እያንዳንዳቸው በእጃቸው የጦር መሣሪያ የያዙ፣ ከተማዪቱን የሚቀጡ ወደዚህ ይምጡ” ብሎ ከፍ ባለ ድምፅ ጮኸ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 በታላቅ ድምፅ በጆሮዬ ጮኸ፥ እንዲህም አለ፦ እያንዳንዳቸው በእጃቸው የጦር ይያዙ፤ ከተማይቱን የሚቀጡ በዚህ ይምጡ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ድምፁን ከፍ አድርጎ “ከተማይቱን የምትቀጡ እናንተ ወደዚህ ቅረቡ፤ ለማጥፋት የተዘጋጀ የጦር መሣሪያዎቻችሁንም ይዛችሁ ኑ!” ብሎ ሲናገር ሰማሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 እርሱም፦ እያንዳንዳቸው የሚያጠፋ መሣሪያን በእጃቸው ይዘው ከተማይቱን የሚቀሥፉ ይቅረቡ ብሎ በታላቅ ድምፅ በጆሮዬ ጮኸ። 参见章节 |