ሕዝቅኤል 8:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 እኔም አየሁ፤ እነሆም ከወገቡ በታች እንደ እሳት የሚመስል የሰው አምሳያ ነበረ፤ ከወገቡም ወደ ላይ እንደ ፀዳል ምሳሌ፥ እንደሚያንጸባርቅ አይነት ነበረ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እኔም አየሁ፤ እነሆ፤ የሰውን ልጅ የሚመስል ነበረ፤ ወገቡ ከሚመስለው ጀምሮ ወደ ታች እንደ እሳት ያለ ነበር፤ ወገቡንም ከሚመስለው ጀምሮ ወደ ላይ እንደ ጋለ ብረት ያበራ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 እኔም አየሁ፥ እነሆም ሰውን የሚመስል ነበረ፥ ወገቡ ከሚመስለው በታች እሳት፥ ከወገቡም በላይ እንደ ብርሃን የሚመስል፥ የሚያንጸባርቅ ነገር የሚመስል ነበረ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ቀና ብዬ ስመለከት መልኩ እንደ እሳት ነበልባል የሚያበራ የሰው አምሳያ አየሁ፤ ያም የሰው አምሳያ ከወገቡ በታች እሳት፥ ከወገቡ በላይ የሚያንጸባርቅ የጋለ ብረት ይመስል ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ እንደ እሳት የሚመስል አምሳያ ነበረ፥ ከወገቡም ምሳሌ ወደ ታች እሳት ነበረ፥ ከወገቡም ምሳሌ ወደ ታች እሳት ነበረ፥ ከወገቡም ወደ ላይ እንደ ፀዳል ምሳሌ፥ እንደሚብለጨለጭም የወርቅ ምሳሌ ነበረ። 参见章节 |