Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እኔም ገባ​ሁና፥ እነሆ በግ​ንቡ ዙሪያ ላይ የተ​ን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች አዕ​ዋ​ፍና እን​ስ​ሳ​ትን ምሳሌ ከን​ቱና ርኩስ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቤት ጣዖ​ታት ሁሉ ተሥ​ለው አየሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እኔም ገብቼ አየሁ፤ እነሆ የሚሳቡ ፍጥረታትና የርኩሳን አራዊት ዐይነት ሁሉ፣ የእስራኤልም ቤት ጣዖታት ሁሉ ዙሪያውን በግንቡ ላይ ተቀርጸው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እኔም ገባሁና አየሁ፥ እነሆ የሁሉም ዓይነት የሚሳቡ ነገሮች፥ የርኩሳን እንስሶች ምስሎችና የእስራኤል ቤት ጣዖታት ሁሉ በግንቡ ዙሪያ ተስለው ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እኔም ወደ ውስጥ ገብቼ ተመለከትኩ፤ በግንቡ ዙሪያ በደረታቸው የሚሳቡ ንጹሕ ያልሆኑ እንስሶችና የእስራኤል ሕዝብ ጣዖቶች ተስሎበት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እኔም ገባሁና እነሆ፥ በግንቡ ዙሪያ ላይ የተንቀሳቃሶችና የርኩሳን አራዊት ምሳሌ የእስራኤልንም ቤት ጣዖታት ሁሉ ተስለው አየሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 8:10
22 交叉引用  

“በላይ በሰ​ማይ ከአ​ለው፥ በታ​ችም በም​ድር ከአ​ለው፥ ከም​ድ​ርም በታች በውኃ ከአ​ለው ነገር የማ​ና​ቸ​ው​ንም ምስል ለአ​ንተ አም​ላክ አታ​ድ​ርግ።


ጠራ​ቢ​ውም እን​ጨት ቈርጦ በልኩ ያቆ​መ​ዋል፤ በማ​ጣ​በ​ቂ​ያም ያያ​ይ​ዘ​ዋል፤ በሰው አም​ሳ​ልና በሰው ውበት ያስ​መ​ስ​ለ​ዋል፤ በቤ​ትም ውስጥ ያቆ​መ​ዋል።


ምድ​ሬ​ንም በተ​ጠሉ በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው ሬሳ​ዎች አር​ክ​ሰ​ዋ​ልና፥ ርስ​ቴ​ንም አስ​ጸ​ያፊ በሆኑ ነገ​ሮች ሞል​ተ​ዋ​ልና አስ​ቀ​ድሜ የበ​ደ​ላ​ቸ​ው​ንና የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


ዝሙ​ቷም ከንቱ ሆነ፤ እር​ስ​ዋም ከድ​ን​ጋ​ይና ከግ​ንድ ጋር አመ​ነ​ዘ​ረች።


“እና​ን​ተና አባ​ቶ​ቻ​ችሁ፥ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ች​ሁም፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ሁም የም​ድ​ርም ሕዝብ በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ ያጠ​ና​ች​ሁ​ትን ዕጣን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሰ​በው፥ በል​ቡም ያኖ​ረው አይ​ደ​ለ​ምን?


በማ​ለ​ዳም ባሪ​ያ​ዎ​ችን ነቢ​ያ​ትን ሁሉ ላክ​ሁ​ባ​ቸው፤ የጠ​ላ​ሁ​ት​ንም ርኩስ ነገር አታ​ድ​ርጉ ብዬ ላክ​ሁ​ባ​ቸው።


በት​እ​ዛዜ አል​ሄ​ዳ​ች​ሁ​ምና፥ ፍር​ዴ​ንም አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምና፥ በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም እን​ደ​ሚ​ኖ​ሩት እንደ አሕ​ዛብ ሕግ አድ​ር​ጋ​ች​ኋል።”


ዳግ​መ​ኛም ዝሙ​ቷን አበ​ዛች፤ በግ​ንብ ላይ የተ​ሣሉ የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሰዎች ሥዕ​ል​ንም አየሁ።


በፊ​ታ​ቸ​ውም ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰባ ሰዎ​ችና የሳ​ፋን ልጅ ያእ​ዛ​ንያ ቆመው ነበር፤ ሰውም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ በእጁ ጥና​ውን ይዞ ነበር፥ የዕ​ጣ​ኑም ጢስ ሽታ ይወጣ ነበር።


እር​ሱም፥ “ግባ፤ በዚህ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ክፉ​ውን ርኵ​ሰት እይ” አለኝ።


የማ​ይ​ሞ​ተ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር በሚ​ሞት ሰውና በዎ​ፎች፥ አራት እግር ባላ​ቸ​ውም፥ በሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ትም መልክ መስ​ለው ለወጡ።


“ርኩ​ስን ነገር ሁሉ አት​ብሉ።


እን​ዳ​ት​በ​ድሉ፥ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል፥ የማ​ና​ቸ​ው​ንም ነገር ምሳሌ፥ በወ​ንድ ወይም በሴት መልክ የተ​ሠ​ራ​ውን፥ በም​ድር ላይ ያለ​ውን፥


በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ሽ​ከ​ረ​ከ​ረ​ውን ሁሉ ምሳሌ፥ ከም​ድ​ርም በታች በውኃ ውስጥ የሚ​ኖ​ረ​ውን የዓ​ሣን ሁሉ ምሳሌ አታ​ድ​ርጉ፤


ከእ​ና​ንተ ጋር የተ​ማ​ማ​ለ​ውን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን እን​ዳ​ት​ረሱ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የከ​ለ​ከ​ለ​ውን፥ በማ​ና​ቸ​ውም ቅርጽ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል እን​ዳ​ታ​ደ​ርጉ እን​ግ​ዲህ ተጠ​ን​ቀቁ።


“ልጆ​ችን፥ የልጅ ልጆ​ች​ንም በወ​ለ​ዳ​ችሁ ጊዜ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም ረዥም ዘመን በተ​ቀ​መ​ጣ​ችሁ ጊዜ፥ በበ​ደ​ላ​ች​ሁም ጊዜ፥ በማ​ና​ቸ​ውም ቅርጽ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል ባደ​ረ​ጋ​ችሁ ጊዜ፥ ታስ​ቈ​ጡ​ትም ዘንድ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ የሆ​ነ​ውን ነገር በሠ​ራ​ችሁ ጊዜ፥


跟着我们:

广告


广告