Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 7:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከእ​ነ​ር​ሱም የሚ​ሸሹ ይድ​ናሉ፤ መብ​ረ​ርን እን​ደ​ሚ​ማር ርግ​ብም በተ​ራራ ላይ ይሆ​ናሉ፤ እኔም በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ሁሉ እገ​ድ​ላ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ተርፈው ያመለጡት ሁሉ በሸለቆ እንደሚኖሩ ርግቦች ስለ ኀጢአታቸው እያለቀሱ በተራራ ላይ ይሆናሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከእነርሱም የሚሸሹ ያመልጣሉ፥ እንደ ሸለቆ እርግቦች በተራራ ላይ ይሆናሉ፥ ሁሉም በኃጢአታቸው ላይ ያቃስታሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የሸለቆ ርግቦች ራሳቸውን ለማዳን ወደ ተራራ እንደሚወጡ እንዲሁም ከሰዎቹ መካከል ከሞት የተረፉ ካሉ በተራራ ላይ ተገኝተው በኃጢአታቸው ምክንያት እንደ ሸለቆ ርግቦች የሐዘን እንጒርጒሮ ያሰማሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከእነርሱም የሚሸሹ ይድናሉ በተራራም ላይ ይሆናሉ፥ እኔም በኃጢአታቸው ሁሉን እገድላለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 7:16
22 交叉引用  

አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው እኛ አም​ል​ጠን ቀር​ተ​ናል፤ እነሆ በፊ​ትህ በበ​ደ​ላ​ችን አለን፤ ስለ​ዚህ በፊ​ትህ ሊቆም የሚ​ችል የለም።”


ሁል​ጊዜ ቀኑን ሁሉ ጠላ​ቶች ረገ​ጡኝ፥ የሚ​ዋ​ጉኝ በዝ​ተ​ዋ​ልና ፈራሁ።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘርን ባያ​ስ​ቀ​ር​ልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆ​ንን፥ እንደ ገሞ​ራም በመ​ሰ​ልን ነበር።


ያመ​ለ​ጠው የይ​ሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰ​ድ​ዳል፤ ወደ ላይም ያፈ​ራል።


እንደ ሸመላ እን​ዲሁ ጮህሁ፤ እንደ ርግ​ብም አጕ​ረ​መ​ረ​ምሁ፤


እንደ ድብና እንደ ርግብ በአ​ን​ድ​ነት ይሄ​ዳሉ፤ ፍር​ድን እን​ጠ​ባ​በቅ ነበር፤ መዳ​ንም የለም፤ ከእ​ኛም ርቆ​አል።


ዐመ​ፃ​ችን በአ​ንተ ፊት በዝ​ቶ​አ​ልና፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንም መስ​ክ​ሮ​ብ​ና​ልና፥ ዐመ​ፃ​ችን ከእኛ ጋር ነውና፥ ጽድ​ቅ​ንም አላ​ወ​ቅ​ን​ምና።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ዐም​ጸ​ዋ​ልና፥ ቅዱስ አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም ረስ​ተ​ዋ​ልና ከብዙ ሰዎች ድምፅ ተሰማ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ልቅ​ሶና ጩኸ​ትም ተሰማ።


እያ​ለ​ቀሱ ሄዱ፤ እኔም በማ​ጽ​ና​ናት አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በወ​ንዝ ዳር በቅን መን​ገድ አስ​ሄ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ር​ሱም አይ​ሰ​ና​ከ​ሉም፤ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል አባት ነኝና፥ ኤፍ​ሬ​ምም በኵሬ ነውና።”


በዚያ ለመ​ቀ​መጥ በል​ባ​ቸው ተስፋ ወደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጓት ወደ ይሁዳ ምድር ይመ​ለሱ ዘንድ በግ​ብፅ ለመ​ኖር ከመጡ ከይ​ሁዳ ቅሬታ ወገን የሚ​ያ​መ​ል​ጥና የሚ​ቀር፥ ወደ​ዚ​ያም የሚ​መ​ለስ አይ​ኖ​ርም፤ ከሚ​ያ​መ​ል​ጥም በቀር ማንም አይ​መ​ለ​ስም።”


ከሰ​ይ​ፍም የሚ​ያ​መ​ልጡ በቍ​ጥር ጥቂ​ቶች ሰዎች ከግ​ብፅ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመ​ለ​ሳሉ፤ ሊቀ​መ​ጡም ወደ ግብፅ ምድር የገ​ቡት የይ​ሁዳ ቅሬታ ሁሉ ከእኔ ወይም ከእ​ነ​ርሱ የማ​ና​ችን ቃል እን​ዲ​ጸና ያው​ቃሉ።


ምድ​ርን ትተ​ና​ልና፥ ቤቶ​ቻ​ች​ን​ንም ጥለን ሄደ​ና​ልና እን​ዴት ጐሰ​ቈ​ልን! እን​ዴት አፈ​ርን! የሚል የል​ቅሶ ድምፅ በጽ​ዮን ተሰ​ም​ቶ​አል።


ነገር ግን እነሆ የሚ​ያ​መ​ል​ጡና ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችን ከእ​ር​ስዋ የሚ​ያ​ወጡ ይቀ​ሩ​ላ​ታል፤ እነሆ ወደ እና​ንተ ይወ​ጣሉ፤ እና​ን​ተም መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንና ሥራ​ቸ​ውን ታያ​ላ​ችሁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ላይ ስላ​መ​ጣ​ሁት ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስላ​መ​ጣ​ሁ​ባ​ትም ነገር ሁሉ ትጽ​ና​ና​ላ​ችሁ፤


በጎች በተ​ራ​ሮች ሁሉና በረ​ዘሙ ኮረ​ብ​ቶች ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነ​ዋል፤ በጎ​ችም በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነ​ዋል፤ የሚ​ፈ​ል​ግም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም።


ክፉ​ውን መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና መል​ካም ያይ​ደ​ለ​ውን ሥራ​ች​ሁ​ንም ታስ​ባ​ላ​ችሁ፤ ስለ በደ​ላ​ች​ሁና ስለ ርኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ራሳ​ች​ሁን ትጸ​የ​ፋ​ላ​ችሁ።


ንግሥት ተገለጠች፥ ተማረከችም፥ ሴቶች ባሪያዎችዋም እንደ ርግብ እየጮኹና ደረታቸውን እየመቱ ዋይ ዋይ ይላሉ።


ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአል፣ የእግዚአብሔር ቀን ድምፅ ቀርቦአል እጅግም ፈጥኖአል፣ ኃያሉም በዚያ በመራራ ልቅሶ ይጮኻል።


跟着我们:

广告


广告