Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 6:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በሩቅ ያለው በቸ​ነ​ፈር ይሞ​ታል፤ በቅ​ር​ብም ያለው በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃል፤ በሀ​ገር የቀ​ረ​ውና የተ​ከ​በ​በ​ውም በራብ ይሞ​ታል፤ እን​ዲሁ መዓ​ቴን እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በሩቅ ያለው በቸነፈር ይሞታል፤ በቅርብ ያለው በሰይፍ ይወድቃል፤ በሕይወት የተረፈውና የዳነው በራብ ያልቃል። መዓቴንም በዚህ ዐይነት ሁኔታ በእነርሱ ላይ እፈጽማለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በሩቅ ያለው በቸነፈር ይሞታል፥ በቅርብ ያለውም በሰይፍ ይወድቃል፥ በሕይወት የተረፈውና የዳነውም በራብ ይሞታል፥ መዓቴን በእነርሱ ላይ እፈጽማለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በሩቅ ያሉት ታመው ይሞታሉ፤ በቅርብ ያሉትም በጦርነት ይገደላሉ፤ ከዚያ የሚተርፉትም በራብ ያልቃሉ፤ በዚህም ዐይነት ኀይል የተሞላበትን ቊጣዬን በእነርሱ ላይ እፈጽማለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በሩቅ ያለው በቸነፈር ይሞታል፥ በቅርብም ያለው በሰይፍ ይወድቃል፥ የቀረውና የዳነውም በራብ ይሞታል፥ እንዲሁ መዓቴን እፈጽምባቸዋለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 6:12
11 交叉引用  

ካህ​ናት ሆይ፥ ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ልቧ የሚ​ገባ ነገ​ርን ተና​ገሩ፤ ውር​ደቷ እንደ ተፈ​ጸመ፥ ኀጢ​አ​ቷም እንደ ተሰ​ረየ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ስለ ኀጢ​አቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀ​በ​ለች አጽ​ና​ኑ​አት።


ለእ​ነ​ርሱ፥ ለዘ​ራ​ቸ​ውና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከሰ​ጠ​ኋ​ቸው ምድር እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሰይ​ፍ​ንና ራብን ቸነ​ፈ​ር​ንም እሰ​ድ​ዳ​ለሁ።”


አሁ​ንም ሄዳ​ችሁ እን​ድ​ት​ቀ​መጡ በወ​ደ​ዳ​ች​ሁ​በት ስፍራ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም እን​ድ​ት​ሞቱ በእ​ር​ግጥ ዕወቁ።”


ካፍ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓ​ቱን ፈጽ​ሞ​አል፤ ጽኑ ቍጣ​ው​ንም አፍ​ስ​ሶ​አል፤ እሳ​ትን በጽ​ዮን ውስጥ አቃ​ጠለ፤ መሠ​ረ​ቷ​ንም በላች።


ታው። የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሆይ፥ በደ​ልሽ ተፈ​ጸመ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ስ​ማ​ር​ክ​ሽም። የኤ​ዶ​ም​ያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ በደ​ል​ሽን ይጐ​በ​ኘ​ዋል፤ ኀጢ​አ​ት​ሽ​ንም ይገ​ል​ጣል።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በባ​ድማ ስፍ​ራ​ዎች ያሉ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ በም​ድረ በዳ ያለ​ውን ለአ​ራ​ዊት መብል አድ​ርጌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ በአ​ም​ባ​ዎ​ችና በዋ​ሻ​ዎች ያሉ በቸ​ነ​ፈር ይሞ​ታሉ።


ከአ​ን​ቺም ሢሶው በቸ​ነ​ፈር ይሞ​ታል፤ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም በራብ ያል​ቃል፤ ሢሶ​ውም በዙ​ሪ​ያሽ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃል፤ ሢሶ​ው​ንም ወደ ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ለሁ፤ በኋ​ላ​ቸ​ውም ሰይ​ፍን እመ​ዝ​ዛ​ለሁ።


“ቍጣ​ዬ​ንና መዓ​ቴ​ንም በእ​ነ​ርሱ ላይ እጨ​ር​ሳ​ለሁ፤ መዓ​ቴ​ንም በፈ​ጸ​ም​ሁ​ባ​ቸው ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ን​ዓቴ እንደ ተና​ገ​ርሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ።


ጊዜው መጥ​ቶ​አል፤ ቀኑ እነሆ ቀር​ቦ​አል፤ መቅ​ሠ​ፍቷ በሁ​ለ​ን​ተ​ናዋ መል​ቶ​አ​ልና የሚ​ገዛ ደስ አይ​በ​ለው፤ የሚ​ሸ​ጥም አይ​ዘን።


ሰይፍ በውጭ፥ ቸነ​ፈ​ርና ራብ በው​ስጥ አለ፤ በሜዳ ያለው በሰ​ይፍ ይሞ​ታል፤ በከ​ተ​ማም ያለ​ውን ቸነ​ፈ​ርና ራብ ይፈ​ጁ​ታል።


跟着我们:

广告


广告