ሕዝቅኤል 5:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 እርስዋም ከአሕዛብ ይልቅ ፍርዴን በኀጢአት ለወጠች፤ በዙሪያዋም ከአሉ ሀገሮች ሁሉ ይልቅ ትእዛዜን ተላለፈች፤ ፍርዴን ጥለዋልና፥ በትእዛዜም አልሄዱምና። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 እርሷም በዙሪያዋ ካሉት አገሮችና አሕዛብ ይልቅ በሕጌና በሥርዐቴ ላይ በክፋቷ ዐመፀች፤ ሕጌን ጥላለች፤ ሥርዐቴንም አልተከተለችም።’ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 እርሷም ከሕዝቦች ይልቅ በትእዛዛቴ ላይ፥ በዙሪያዋ ካሉ አገሮችም ሁሉ ይልቅ በሕጌ ላይ በክፋቷ አምፃለች፥ እነርሱ ትእዛዛቴን አንቀበልም ብለዋልና፥ በሕጌም አልኖሩምና። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ኢየሩሳሌም ግን ሕጎቼንና ደንቤን በመጣስ ከሌሎች ሕዝቦች ይልቅ የከፋችና በዙሪያዋም ካሉት አገሮች ይበልጥ እምቢተኛ መሆንዋን አሳይታለች፤ ኢየሩሳሌም ሕጎቼንና ደንቦቼን ንቃለች፤ ትእዛዞቼንም አልተከተለችም።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 እርስዋም ከአሕዛብ ይልቅ ፍርዴን በኃጢአት ለወጠች በዙሪያዋም ካሉ አገሮች ሁሉ ይልቅ ትእዛዜን ተላለፈች፥ ፍርዴን ጥለዋልና፥ በትእዛዜም አልሄዱምና። 参见章节 |