Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 48:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 “ከይ​ሁ​ዳም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለመባ የተ​ለየ ክፍል ይሆ​ናል፤ ወርዱ ሃያ አም​ስት ሺህ ክንድ ይሆ​ናል፤ ርዝ​መ​ቱም ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ከዕጣ ክፍ​ሎች እንደ አንዱ ይሆ​ናል፤ ቤተ መቅ​ደ​ሱም በመ​ካ​ከሉ ይሆ​ናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ይሁዳን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የሚያዋስነው ምድር ለመባ የሚቀርብ ድርሻ ይሆናል፤ ስፋቱም ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ነው፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያለውም ርዝመቱ፣ ከነገዶቹ ድርሻ እንደ አንዱ ሆኖ፣ መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከይሁዳ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለምታቀርቡት መባ የሚሆን ድርሻ ይሆናል፤ ወርዱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል፥ ርዝመቱም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል፥ ከድርሻዎቹ እንደ አንዱ ይሆናል፥ መቅደሱም በመካከሉ ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከይሁዳ ነገድ ድንበር ጋር የተያያዘ ቦታ ለይታችሁ ትመደባላችሁ፤ ይህም ቦታ ወርዱ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመት ከሌሎች ነገዶች ድርሻ ጋር ከምሥራቅ ጐን እስከ ምዕራብ ጐን ድረስ እኩል ይሆናል፤ ቤተ መቅደሱም የሚገኘው በዚህ ቦታ መካከል ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ከይሁዳም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለመባ የሆነ የዕጣ ክፍል ይሆናል፥ ወርዱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል ርዝመቱም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ከዕጣ ክፍሎች እንደ አንዱ ይሆናል፥ መቅደሱም በመካከሉ ይሆናል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 48:8
13 交叉引用  

አንቺ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ ሐሤ​ትም አድ​ርጊ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ በመ​ካ​ከ​ልሽ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና።”


“በተ​ቀ​ደ​ሰው መባና በከ​ተ​ማ​ዪቱ ይዞታ፥ በዚ​ህና በዚያ ወገን የቀ​ረው ለአ​ለ​ቃው ይሆ​ናል፤ በመ​ባው በሃያ አም​ስት ሺህ ፊት እስከ ምሥ​ራቁ ድን​በር፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል በሃያ አም​ስት ሺህ ፊት እስከ ምዕ​ራቡ ድን​በር፥ እንደ ዕጣ ክፍል ሁሉ መጠን፥ ለአ​ለ​ቃው ይሆ​ናል፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም መባና ቤተ መቅ​ደሱ በመ​ካ​ከሉ ይሆ​ናል።


ዙሪ​ያ​ዋም ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ክንድ ይሆ​ናል፥ ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ስም፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ አለ’ ተብሎ ይጠ​ራል።”


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ት​ለ​ዩት መባ ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ ወር​ዱም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆ​ናል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦ​ትስ በጣ​ዖት ቤት ውስጥ የሚ​ያ​ኖር ማን ነው? የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪ​ያ​ዎች እኛ አይ​ደ​ለ​ን​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፥ “እኔ በእ​ነ​ርሱ አድ​ራ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እኖ​ራ​ለሁ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል።”


በእ​ርሱ ፍጹም መለ​ኮቱ በሥጋ ተገ​ልጦ ይኖ​ራ​ልና።


ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ መቅደስዋ ናቸውና መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።


ታላቅም ድምፅ ከሰማይ “እነሆ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው፤ ከእነርሱም ጋር ያድራል፤ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤


ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፤ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፤ ፊቱንም ያያሉ፤


跟着我们:

广告


广告