Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 48:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 “በተ​ቀ​ደ​ሰው መባና በከ​ተ​ማ​ዪቱ ይዞታ፥ በዚ​ህና በዚያ ወገን የቀ​ረው ለአ​ለ​ቃው ይሆ​ናል፤ በመ​ባው በሃያ አም​ስት ሺህ ፊት እስከ ምሥ​ራቁ ድን​በር፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል በሃያ አም​ስት ሺህ ፊት እስከ ምዕ​ራቡ ድን​በር፥ እንደ ዕጣ ክፍል ሁሉ መጠን፥ ለአ​ለ​ቃው ይሆ​ናል፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም መባና ቤተ መቅ​ደሱ በመ​ካ​ከሉ ይሆ​ናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “በተቀደሰው ድርሻና በከተማዪቱ ቦታ ግራና ቀኝ ያለው ቀሪ ቦታ፣ ለገዢው ይሆናል፤ ይህም ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ከሆነው ከተቀደሰው ቦታ አንሥቶ በምሥራቅ በኩል እስከ ምሥራቁ ወሰን ይዘልቃል፤ በምዕራቡም በኩል እንዲሁ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ከሆነው ይዞታ አንሥቶ እስከ ምዕራቡ ወሰን ይዘልቃል። የየነገዱ ድርሻ ከሆነውም መሬት ጐን ለጐን የሚሄዱት ቦታዎች የገዢው ይሆናሉ። የተቀደሰው ቦታና መቅደሱ በመካከላቸው ይሆናሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ በዚህና በዚያ ወገን የቀረው ለአለቃው ይሆናል፤ በመባው በሃያ አምስቱ ሺህ ፊት ወደ ምሥራቁ ድንበር፥ በምዕራብም በኩል በሀያ አምስቱ ሺህ ፊት ወደ ምዕራቡ ድንበር፥ እንደ ዕጣ ክፍሎች ሁሉ መጠን፥ ለአለቃው ይሆናል፤ የተቀደሰውም መባና ቤተ መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በተቀደሰው ቦታና በከተማውም ይዞታ በሁለቱም በኩል የተረፈው ክፍል የመስፍኑ ድርሻ ነው። ይኸውም በምሥራቅ በኩል የተቀደሰውን ቦታ ከሚያዋስነው ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ተነሥቶ እስከ ምድሪቱ ወሰን ድረስ ነው። በምዕራብም በኩል የተቀደሰውን ቦታ ከሚያዋስነው ከኻያ አምስት ሺህ ክንድ ተነሥቶ እስከ ምድሪቱ ወሰን ድረስ ነው። የመሪውም ድርሻ ርዝመቱ ከሌሎቹ ነገዶች ድርሻ እኩል ነው። በዚህ ዐይነት የተቀደሰው ቦታና ቤተ መቅደሱ በመካከል ይሆናሉ ማለት ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ በዚህና በዚያ ወገን የቀረው ለአለቃው ይሆናል፥ በመባው በሃያ አምስቱ ሺህ ፊት ወደ ምሥራቁ ድንበር፥ በምዕራብም በኩል በሀያ አምስቱ ሺህ ፊት ወደ ምዕራቡ ድንበር፥ እንደ ዕጣ ክፍል ሁሉ መጠን፥ ለአለቃው ይሆናል፥ የተቀደሰውም መባና ቤተ መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 48:21
8 交叉引用  

“ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት በላ​ያ​ቸው ንጉሥ ይሆ​ናል፤ ለሁ​ሉም አንድ እረኛ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ በፍ​ር​ዴም ይሄ​ዳሉ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ይጠ​ብ​ቃሉ፤ ያደ​ር​ጓ​ት​ማል።


የመ​ቅ​ደ​ሱም ቀዳ​ም​ያት ለካ​ህ​ናቱ ይሆ​ናል፤ በሰ​ሜን በኩል ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በደ​ቡ​ብም በኩል ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ ክንድ ይሆ​ናል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤተ መቅ​ደስ በመ​ካ​ከሉ ይሆ​ናል።


መባው ሁሉ ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ሺህ ክንድ ይሆ​ናል፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን መባ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ይዞታ ጋር አራት ማዕ​ዘን አድ​ር​ጋ​ችሁ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።


የሌ​ዋ​ው​ያን ርስት፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ይዞታ ለአ​ለ​ቃው በሆ​ነው መካ​ከል ይሆ​ናል፤ በይ​ሁዳ ድን​በ​ርና በብ​ን​ያም ድን​በር መካ​ከል የአ​ለ​ቃው ዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።


“ከይ​ሁ​ዳም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለመባ የተ​ለየ ክፍል ይሆ​ናል፤ ወርዱ ሃያ አም​ስት ሺህ ክንድ ይሆ​ናል፤ ርዝ​መ​ቱም ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ከዕጣ ክፍ​ሎች እንደ አንዱ ይሆ​ናል፤ ቤተ መቅ​ደ​ሱም በመ​ካ​ከሉ ይሆ​ናል።


የይ​ሁዳ ልጆ​ችና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በአ​ን​ድ​ነት ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም አንድ አለቃ ይሾ​ማሉ፤ ከም​ድ​ሪ​ቱም ይወ​ጣሉ፤ የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ቀን ታላቅ ይሆ​ና​ልና።


跟着我们:

广告


广告