Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 48:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በሃያ አም​ስቱ ሺህ አን​ጻር አም​ስት ሺህ ወርድ ያለው የቀረ ቅዱስ ያይ​ደለ ስፍራ ለከ​ተ​ማ​ዪቱ ለጋራ ጉዳ​ይዋ፥ ለመ​ኖ​ሪያ፥ ለማ​ሰ​ማ​ር​ያም ይሆ​ናል፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም በመ​ካ​ከሉ ትሆ​ና​ለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “ዐምስት ሺሕ ክንድ ወርድና ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ርዝመት ያለው የቀረው ቦታ ለከተማዪቱ የጋራ ጥቅም፣ ለቤት ሥራና ለከብት ማሰማሪያ ይውላል፤ ከተማዪቱም በመካከሉ ትሆናለች፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በሀያ አምስቱ ሺህ ፊት ለፊት አምስት ሺህ ወርድ ያለው የቀረ ስፍራ ለከተማይቱ ለጋራ ጉዳይዋ፥ ለመኖሪያና ለማሰማርያ ይሆናል፤ ከተማይቱም በመካከሉ ትሆናለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ልዩ ከሆነው ክልል ተከፍሎ የሚቀረው ስፍራ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመት አምስት ሺህ ክንድ ወርድ ነው፤ እርሱም በአጠቃላይ ለሕዝቡ የጋራ መጠቀሚያ ይሆናል፤ ለቤት ሥራና ለከብት ማሰማሪያም ይሆናል፤ ከተማይቱም በመካከሉ ትሆናለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በሀያ አምስቱም ሺህ አንጻር አምስት ሺህ ወርድ ያለው የቀረ ስፍራ ለከተማይቱ ለጋራ ጉዳይዋ፥ ለመኖሪያ ለማሰማርያም ይሆናል፥ ከተማይቱም በመካከሉ ትሆናለች።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 48:15
5 交叉引用  

ካህ​ና​ቷም ሕጌን ጣሱ፤ በመ​ቅ​ደ​ሴም መካ​ከል ቅድ​ሳ​ቴን አረ​ከሱ፤ ከር​ኵ​ሰ​ትም አል​ራ​ቁም፤ በን​ጹ​ሕና በር​ኩስ መካ​ከል ያለ​ው​ንም ልዩ​ነት አላ​ወ​ቁም፤ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ከሰ​ን​በ​ታቴ ሸፈኑ፤ እኔም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ረከ​ስሁ።


በአ​ራ​ቱም ወገን ለካ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንና ያል​ተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ይለይ ዘንድ ርዝ​መቱ አም​ስት መቶ ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት መቶ ክንድ የሆነ ቅጥር በዙ​ሪ​ያው ነበረ።


በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውና ባል​ተ​ቀ​ደ​ሰው መካ​ከል ይለዩ ዘንድ ሕዝ​ቤን ያስ​ተ​ምሩ፤ ንጹ​ሕና ንጹሕ ባል​ሆ​ነው መካ​ከል ይለዩ ዘንድ ያሳ​ዩ​አ​ቸው።


“ለከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ይዞታ በተ​ቀ​ደ​ሰው የዕጣ ክፍል መባ አጠ​ገብ ወርዱ አም​ስት ሺህ፥ ርዝ​መ​ቱም ሃያ አም​ስት ሺህ የሆ​ነ​ውን ስፍራ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ። እር​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ይሆ​ናል።


ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።


跟着我们:

广告


广告